ሕይወትን እንደአመጣጡ መቀበልን ተማር

ስለዚህ ለነገ በማሰብ አትጨነቁ፤ የነገ ጭንቀት ለነገ ይደር፤ እያንዳንዱ ዕለት የራሱ የሆነ በቂ ችግር አለዉና፡፡ – ማቴ 6:34

ክ እንደ አብዛኛዉ ህዝብ የማልወዳቸዉንና ምንም ማድረግ የማልችልባቸዉን ነገሮች እቋቋማለሁ፡፡ አንድ ቀን ጌታ እንዲህ አለኝ “ጆይስ ህይወትን እንደአመጣጡ መቀበልን ተማሪ።”

ይህ ለሁላችንም ትምህርት እንደሚሆን አምናለሁ፡፡ እርሱ እያለኝ የነበረዉ ምንም ማድረግ የማልችልባቸዉን ነገሮች መፋለም ማቆም እንዳለብኝ ነዉ፡፡

ወደ አንድ ቦታ እየተጓዝን በአደጋ ወይም በከባድ የአየር ሁኔታ ምክንያት በተጨናነቀ ትራፊክ ዉስጥ ድንገት ራሳችንን ብናገኝ፤ ያንን ነገር መቋቋም አንዳች አያደርግልንም፡፡ ጊዜና የእግዚአብሔር ጣልቃ ገብነት ብቻ ናቸዉ ሁኔታዉን መለወጥ የሚችሉት፡፡ ታዲያ ለምን ዘና አትልም እና ጊዜዉን ተደስቶ ለማሳለፍ አንድ ነገር ለመፈለግ አትጥርም?

እግዚአብሔር ህይወትን እንደየአመጣጡ እንድንይዝ አስታጥቆናል ለዚያም ነዉ ዛሬ ላይ ብቻ እንድናተኩር የተናገረን፡፡ ከቁጥጥራችን ዉጪ ስለሆኑ ነገሮች እየተጨነቅን ጊዜ የምናጠፋ ከሆነ እንደምንደክምና ተስፋ ወደ መቁረጥ እንደምንደርስ እርሱ ያዉቃል፡፡

ከቁጥጥርህ ዉጪ የሆኑ ነገሮችን ለመለወጥና ለመቆጣጠር በመሞከር ጊዜህን ማጥፋት አያስፈልግህም፡፡ አእምሮህን እግዚአብሔር በፊትህ ያስቀመጠዉን ነገር ለመስራት አዘጋጅ ስለቀሪዉ እርሱ ይጨነቅበታል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

ጌታ ሆይ! ሁሉን ነገር መቆጣጠር እንደማልችል ግን አንተን ማመን እንደምችል አስተዉያለሁ፡፡ አሁን አንተ የሰጠሀኝን ሁሉ በተቻለኝ አቅም ሁሉ ለመስራትና ቀሪዉን ለአንተ ለመተዉ ዉሳኔ አደርጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon