በመናዘዝ ፀልይ

በመናዘዝ ፀልይ

እርስ በርሳቸው በኃጥያታችሁ ተናዘዘ ትፈውሱም ዘንድ እያንዳንዱ ስለሌላው ይፀልይ የጻድቅ ሰው ፀሎት በሥራዋ እጅግ ኃይል ታደርጋለች፡፡ ያዕ 5÷16

ኃጥያት ከእግዚአብሔር ይለየናል፡፡ እግዚአብሔር ከእኛ የራቀ ዓይነት ስሜት እንዲሰማን ያደርጋል፡፡ እኛ እራሳችንን ከእግዚአብሔር እንድንሰውር ወይ ደግሞ ወደ እርሱ ቀርበን እንዳንነግረው ያ ደግሞ እኛ ወደ እርሱ ቀርበን የእርሱን ድምፅ እንዳንሰማ ይከልለናል፡፡ ኃጥያት እንዳደረግን ስታውቀን ወደ እግዚአብሔር ቀርበን የእርሱን ይቅርታ ስንጠይቅ እሱ ደግሞ ይቀበለናል፡፡ ምክንያቱም እርሱ እኛ በኃጥያታችን ስንናዘዝ ይቅር ሊለን ተስፋ ሰጥቶናል፡፡ የተሰወሩ ነገሮች በሕይወታችን ኃይልና ተጽዕኖ ስላላቸው አንዳንድ ጊዜ ኃጥያታችንን ሌሎች ሰዎች መናዘዝ እንደዛሬው ጥቅስ መሠረት በጣም ይጠቅሙናል፡፡

ስህተታችንን ለሆነ ሰው መናዘዝና ለፀሎት ለመጠየቅ በመጀመሪያ የሚያስፈልገው ግለሰቡን በመጀመሪያ መታመንን እና ትኩረታችንን ወደጎን አድርገን በትህትና ትግላችንና ተጋድሎአችንን መካፈልን የሚጠይቅ ነው፡፡ እንዲህ ማድረግ የሚከብድህ ከሆነ እግዚአብሔር በትህትና እንድታደርግ እንዲረዳህ ጠይቅ፡፡ ምክንያቱም የሚታመን ጓደኛ ካገኘ ውጤቱ በጣም አስገራሚ ስለሚሆን ነው፡፡ ከሰውየው ጋር እየተቸገርክ ያለበትን በማካፈል ‹‹እኔ እንዲህ አይነት ችግር አለብኝና ከዚህ ነገር ነፃ መሆን እፈልጋለሁ፣ እኔ እየተጓዳውበት ነውና በዚህ ጉዳይ እንድትፀልይልን እፈልጋለሁ›› ትለዋለህ፡፡

አስታውሳለሁ አንድ ወቅት በጓደኛዬ ላይ ቅናት አስቸገረኝና እንዲወገድልኝ ፀለይኩ፡፡ ነገር ግን በክፉኛ ቅናቱ ባሰብኝ፡፡ ስለዚህ ለባለቤቴ ዴቭ ተናዘዝኩና እንዲፀልይልኝ ጠየኩት፡፡ ወደ ውጭ አወጣሁትና ኃይሉን ከላዬ በመስበር ከዚያ ነገር እራሴን ነፃ አወጣሁት፡፡ ሁልጊዜ በመጀመሪያ እራስህ ወደ እግዚአብሔር ቅረብ፣ ነገር ግን እረዳት የሚያስፈልግህ ከሆነ ወደ ጓደኛህ ወይም ወደ መንፈሣዊ መሪ ሂድ፣ እራስን ዝቅ አለማድረግ በመንገድህ ልቆም አይገባም፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ኩራት ለሌሎች መናዘዝን ባስፈለገህ ጊዜ በፊትህ ቆሞ ሊያግድህ አይገባም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon