መናፍስትን የመለየት ሥጦታ

መናፍስትን የመለየት ሥጦታ

ለአንዱም መናፍስትን የመለየት …… 1ቆሮ 12÷ 10

መናፍስትን የመለየት ሥጦታ እጅግ በጣም ጠቃሚ እንደሆነ አምናለሁ እና አንተም እንድትሻውና እንድታሳድገው አበረታታለሁ፡፡ አንዳንድ ሰዎች መናፍስትን የመለየት ሥጦታ እግዚአብሔር ሲፈቅድ ከተፈጥሮ በላይ የሆነ እይታ በመንፈሳዊ ዓለም ውስጥ ይሰጣቸዋል ይላሉ፡፡ ብዙዎች ደግሞ የመናፍስት መለየት ሥጦታ የሚሰጠው የሰውዬውን እውነተኛ ተፈጥሮ ወይም ስለሁኔታ እንድናውቅ ነው ብሎ ያምናሉ፡፡ አለማችን በብዙ ማታለሎች የተሞላች ናት፡፡ ብዙ ሰዎች ከውጭ እንደምታዩት ዓይነት አይደሉም፡፡ መናፍስትን የመለየት ሥጦታም ሰዎች ከተሸፈኑበት መሸፈኛ (ማክስ) ጀርባ ያላቸውን እውነተኛ ማንነትና ምን እየተካሄደ እንዳለ ለማወቅ ይረዳናል፡፡ ስጦታው በተጨማሪም የሆነ ነገር ሲሆን ጥሩ መሆኑንና የሰዎች ልብ መልካም መሆኑንና አለመሆኑን ለመረዳት ያስችላል፡፡

ዴቭ (ባለቤቴና) እኔ ሰዎች በእኛ አገልግሎት አብሮን ሊሰሩ ሲያናግሩን ይህ ስጦታ ብዙ ጊዜ ተለማምደናል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ ሰዎች አብሮን ለመሥራት የሚሠሩትን የሥራ ዓይነት ብቃት፣ ችሎታ፣ ጽናታቸውን የተዋጣለት ያስመስላሉ፡፡ በሆነ ምክንያት ከሆነ ሰው ጋር ተገናኘንና እርሱን ለመቅጠር ብለን ሁሉም ሰው ተሳተፈበት፣ ነገር ግን በልብ ውስጥ ሰላም የሚነሣኝና ነገሩን ማድረግ እንደሌለብን ተሰማኝ፡፡ ሆኖም ግን እንደምንም ብለን ስንቀጥረው ምንም አዲስ ነገር አልሰራም ነገር ግን ሁከት አስነሳ፡፡ እኔም ከውጭ ባሉት ሥራዎች እንድሰራ አደረኩት ምን እንደፈለገ ለማወቅ ብለን በመለየት ፀጋ እየተረዳው ሳለው ባለማድረግ መሠራት የሌለበትን ስህተት (ግድፈት) እንደ ስራው ከዚያ በኋላ ተረዳው፡፡

የእግዚአብሔር መንፈስ በልባችን ውስጥ ሆኖ ለልባችን ይናገራል፡፡ ለአእምሮአችን አይደለም የምንነግረው፡፡ የእርሱ ሥጦታ የአእምሮ ወይም የማሰብና የመመራመር እንዲሁም ደግሞ የአእምሮ ተግባር አይደለም መንፈሳዊና በመንፈስ የሚተገበሩ ናቸው፡፡ በመንፈሳችን የሚሰማንን መከተል አለብን፡፡ በአእምሮቸአችን የምናስበው አይደለም ትክክለኛው ስለዚህ ነው እግዚአብሔር የመለየትን ሥጦታ የሰጠን፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- ለመለየት እንድትችል ተማር በምታየውና በምታስበው ብቻ ላይ ተመስርተህ ውሳኔ አታድርግ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon