መንፈስን አታጥፉ

መንፈስ [ቅዱስ]ን አታጥፉ (አታፍኑ ወይም አትያዙ) ። (1 ተሰሎንቄ 5:19)

የዛሬው ክፍል መንፈስ ቅዱስን እንዳናጠፋ ይነግረናል። መንፈስ ቅዱስን የምናጠፋበት አንዱ መንገድ በማማረር እንደሆነ አምናለሁ። በሕይወታችን ውስጥ እንዲሠራ መንፈስ ቅዱስ ያስፈልገናል፣ ደግሞም ማጉረምረም ለማቆም እና አመስጋኝ ለመሆን (የማማረር ተቃራኒ) የበለጠ በመረጥን መጠን መንፈስ ቅዱስ በሁኔታዎቻችን ውስጥ ለመሥራት የበለጠ ነፃነት ይኖረዋል። ማማረር ተፈጥሯዊ ነው፤ በሁኔታዎች መካከል ስንፈተሽ እና ስንሞከር ማመስገን ከተፈጥሮ በላይ ነው። የሚያጉረመርሙ እና የሚያማርሩ ሰዎች እግዚአብሔርን አይሰሙም ምክንያቱም እርሱን ለመስማት ማማረር ማቆም አለባቸው! ይህንን እውነት ለመረዳት ዓመታት ፈጅቶብኛል! አጉረመረምኩ እና አማረርኩ ደግሞም ተማረርኩ፤ በሁሉም ነገር እና በሁሉም ሰው ላይ ስህተት አገኘሁ፣ ከዚያ በኋላ ቅናት አደረብኝ ምክንያቱም በዙሪያዬ ያሉት ሁሉ ከእግዚአብሔር ይሰማሉ እኔ ግን አልሰማም ነበር!

“”ለምንድን ነው መልካም ነገር ለእኔ የማይሆነው?”” አቃሰትኩ። ዴቭ ደጋግማ እንዲ አለችኝ፣ “ጆይስ፣ ነገሮች በአንቺ መንገድ በማይሄዱበት ቁጥር መበሳጨትሽን እስክታቆሚ ድረስ በሕይወታችን ውስጥ መልካም ነገሮች አይከሰቱም።

ያንን ስለነገረኝ ከዚያ ተቆጥቼ “በቃ ስሜቴን አታውቅም ወይም ግድ የለህም!” ብዬ ወደኋላ እመለስ ነበር።

ችግሩ ስለተሰማኝ ነገር ያንን ያህል በጣም ስለጨተነቅኩ እና እግዚአብሔር የገባልኝ ቃል እኔን ለመርዳት በቂ እንደሆነ አለማሰቤ ነበር። እግዚአብሔር በችግራችን ውስጥ እኛን ለመርዳት እና በፈተናዎች ወቅት ታጋሽ ከሆንን (ጥሩ አመለካከት ካለን) ምን ማድረግ እንዳለብን ያሳየናል። ማማረር የትዕግስት ምልክት አይደለም፣ነገር ግን ምስጋና እና ውዳሴ ናቸው። ከስሜቴ ይልቅ በእግዚአብሔር ቃል ለመኖር እንደተማርኩ የእግዚአብሔርን ድምፅ በግልፅ ሰማሁት። ማማረር ለጠላት በር ይከፍታል፣ ነገር ግን ምስጋና እና ውዳሴ ለእግዚአብሔር በር ይከፍታል።


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ በማማረር መንፈስ ቅዱስን አታጥፋ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon