ራስን የመግዛትን ዋጋ መጋፈጥ

ራስን የመግዛትን ዋጋ መጋፈጥ

በተስፋ ደስተኞች ሁኑ፤በመከራ ታገሱ፤በጸሎት ጽኑ፡፡ – ሮሜ 12፡12

እንደ ክርስቲያኖች ብዙዎቻችን ክርስቲያን ስለሆንን ብቻ በሕይወታችን ያለው ማናቸውም ነገር ፍጹም ሊሆን ይገባል የሚል አስተሳሰብ አለን፡፡ነገር ግን ክርስቶስ በግልጹ አስጠንቅቆናል፣…በዚህ ምድር ሳላችሁ መከራ አለባችሁ…(ዮሐ.16፡33)

ኢየሱስ ከአለማዊ ችግሮች ጋር መጋፈጥ እንዳለብን ተናግሯል፡፡እሱን ለመከተል ብለን ራስ ወዳድ የሆኑ ፍላጎታችንን ስንጥል ሁላችን የምንጋፈጣቸው የህይወት ክፍል ናቸው፡፡

ሐዋሪያው ጳውሎስ ነገር ግን ለሌሎች ከሰበክሁ በኋላ እኔ እራሴ ውድቅ ሆኜ እንዳልቀር ፣ሰውነቴን እየጎሰምሁ እንዲገዛልኝ አደርገዋለሁ…ሲል ጽፏል (1ኛ ቆሮ.9፡27)፡፡

ጳውሎ እዚህጋ እየተናገረ ያለው ስለ ራስን መግዛት ነው፡፡ራስን መግዛት ማለት የሀጢያት ፍላጎታችንን ጥለን ምንም ያህል ዋጋ ቢያስከፍለንም በእግዚአብሔር ጸጋ ትክክለኛውን ነገር ማድረግ ነው፡፡

ሁልጊዜ ቀላል አይደለም፡፡ለራስ መሞት የግድ የሚያመጣው የራሱ ስቃይ አለው፣ነገር ግን አስታውሱ በመከራ ፊትም እንኳ ተስፋ አለ ክርስቶስ አለምን አሸንፏልና! ልክ ጳውሎስ እንዳለው በተስፋ ልንደሰት፣በመከራ ልንጸናና በጸሎት ልንተጋ ይገባል፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ስጋዬ ተደሰተም አልተደሰተም አስቀድሜ አንተን ለማስደሰት ወስኛለሁ፡፡ፈቃድህን ለመፈጸም መሰቃየት ቢኖርብኝ እንኳ መንፈስህ በውስጤ ስላለ እና አንተ ደግሞ አለምን ስላሸነፍክ ተስፋ እንዳለኝ አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon