ትእዛዛትህ ሁሉ ጽድቅናቸውና አንደበቴ ቃልህን ተናገረ።(መዝ119:172 )
የእግዚአብሔር ቃል ዉድ የሆነ ሀብት ነዉ፡፡ አላማ-መር የሆነ ህይወት ፣ በብርታትና በስኬት እንድንኖር፣ በጥበብ፣ በምሪት፣ በእዉነትና በህይወታችን በሚያስፈልጉን ነገሮች የተሞላ ነዉ፡፡
በጸሎቶቻችን ሁሉ የእግዚአብሔርን ቃል ማካተትና በእያንዳንዱ ሁኔታዎች ቃሉን መናገር ይኖርብናል፡፡ ቃሉን ማናገር ማለት ቃሉ ራሱ እንደሚለዉ፣ ቃሉን ስንናገር፣ እግዚአብሔር ራሱ የሚለዉን መናገር
ማለት ሲሆን፤ ራሳችንን ከእሱ ጋር እያስማማን ነዉ ማለት ይቻላል፡፡ ጥልቀት ያለዉና አንጸባራቂ የሆነ ግንኙነት ከእግዚአብሔር ጋር መመስረት ከፈለግን፣ ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት ያለብን ሲሆን፤ ቃሉን ከመናገር ሌላ ይህንንም እንድንሆን የሚያደርገን የለም፡፡ ቃሉን መናገራችን የቃሉ እዉቀት እንዲኖረንና በእሱ ላይ ያለንን እምነት ያጠናክራል፡፡ ይህ ድግሞ ጸሎታችን ትክክለኛና ዉጤት ያለዉ እነዲሆን ደርጋል፡፡
ቃሉን ለመናገር፣ የቃሉ እዉቀት ሊኖረን ይገባል፣ ምክንያቱም ከእግዚአብሔር ጋር መስማማት የምንችለዉ እሱ ምንእንዳለና ምን እንደሰራ ስናዉቅ ብቻ ነዉ፡፡ ብዙ ጊዜ ያላቸዉን ነገር፣ የሆኑትን እንዲሆኑ እግዚአብሔርን የሚጠይቁ ሰዎች ያጋጥሙኛል፣ እናም ለነዚህ ሰዎች፣ “እንደዚህ አትጸልዩ! እግዚአብሔር አስቀድሞ እየለመናችሁ ያለዉን ነገር ፈጽሟል፡፡” እግዚአብሄር እንዲባርካችሁ አትለምኑ ምክንያቱም ባርኳችኋል፡፡” ከዚያ ይልቅ “እግዚአብሔር ሆይ፣ እንደቃልህ ስለተባረክሁ አመሰግንሀለሁ” በሉ፡፡ እግዚአብሐየር ሰጥቶን ሳለ እንዲሰጠን መጸለይ አግባብነት የለዉም፡፡ የእግዚአብሔርን ቃል መልሰን በምንጸልይበትና በምናስታዉስበት ጊዜ ቃሉን እያከበርንና ምን እንደሚልም ለራሳችን እያስታወስን ነዉ፡፡ቃሉን በምንናገርበት ጊዜ ሁሉ፣ ምድር ላይ ለዉጥ ሊያመጣ የሚችል ኃይል ከሰማይ ይለቀቃል፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ ከአፋችሁ በእምነት የሚወጣዉ የእግዚአብሔር ቃል ከሁሉም የላቀ በሰማይና በምድርላይ ኃይልና ጉልበትያለዉ ነዉ፡፡