በቅድሚያ አስብበት

ይህንም የምክደው ከሌለ ደና እንድትሉና አንዳች በችኮላ እንዳታደርጉ ይገባል፡፡ የሐዋ. 19 36

አንድን ነገር ከማድረግ በፊት እግዚአብሔርን አለመጠየቅም ሆነ እርሱ ስለ ጉዳዩ እስኪናገረን ድረስ አለመጠበቅ እንዲሁም ዘሎ ወደ ነገሩ ሳናስብበት ልናደርገውን ማድረግ የማይመክርና ስህተት ስሆን ውጤቱም በፀፀትና በተስፋ መቁረጥ ላይ ይጥላል፡፡ አብዛኛውን ጊዜ እራሳችንን በብዙ ነገር እናጨናንቅና አስገድደን በምናደርገው ነገር ውጤት ዝለትና ተስፋ የሌለው ይሆናል፡፡ እግዚአብሔር ብዙውን ጊዜ በመንፈሱ ያበረታታናል፡፡ ነገር ግን ከፈቃዱ ውጭ በሆነ ነገር ላይ ለእኛ ብርታት አይሰጠንም፡፡ በሞኝነታችንም በምናደርገው ነገር ብርታት አይሰጠንም፡፡ አንድን ነገር ለማድረግ ስንወስን እግዚአብሔር ቃላችንን እንድንጠብቅና ታማኞች እንድንሆን ይፈልጋል፡፡ ስለዚህ እርሱ ለእኛ ያለው ምክር በዛሬው ጥቅስ ውስጥ ያለው ስሆን እርሱም ‹‹ከመናገርህ በፊት አስብበት›› የሚል ነው፡፡ በሃሣባችንም ውስጥ የእግዚአብሔር ፈቃድና ምክር ምን እንደሆነ መጠየቅ አለብን፡፡

በዚህ ጉዳይ ላይ ብዙ ከስህተቱ የተማርኩበት የእራሴ የሕይወት ተሞክሮ አሉኝ፡፡ የእግዚአብሔር ምክርና ፈቃድ ሳይጠይቅ አንዳንድ ነገሮች ከፍተኛ ፍላጎት ስላደረብኝ ብቻ በማደርግበት ወቅት አቅጄ የነበርኩት ፍጻሜው ጭቅጭቅና ውጤት አልባ ይሆንብኝ ነበር፡፡ እግዚአብሔርም በእርሱ ምክርና ፈቃድ እንዲሁም ምርት መሄድ አለመሄድን ከነገሮች ውጤት እንዲማር ይተወኝ ነበር፡፡ በእርሱ ምክርና ምርት የተደረጉት ደግሞ ከጭንቀትና ከተስፋ መቁረጥ ያድናል፡፡

የምትሳተፍባቸው ነገሮች አስደሳችና አስፈላጊዎች የሆኑ ብዙ እድሎችና ተስፋ እንደሚሰጡህ እርግጠኛ ነኝ፡፡ ዛሬ በቀላሉ የማበረታታህ ማንኛውንም ነገር የእግዚአብሔርን ፈቀድ ምክርና ምሪት አጥብቀህ በመፈለግ እርሱ አድርግ ወይም አታድርግ ሳይልህ ምንም እርምጃ እንዳትወስድ ነው፡፡


ዛሬ እግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ‹‹ከመናገርህ በፊት አስብ! ›› የሚል ነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon