በትዕግስት ጠብቅ

በትዕግስት ጠብቅ

የመንፈስ ፍሬ ግን ፍቅር፣ ደስታ፣ ሰላም፣ ትዕግሥት፣ ቸርነት፣ በጎነት፣ ታማኝነት፣ – ገላ 5፡22

በህይወታችን ለውጥን ማየት እንሻለን ይሁንና ሁልጊዜም ቢሆን ለውጡ የሚፈልገውን ሂደት ግን መጓዝ አንፈልግም፡፡አንዳንድ ጊዜ ከምናስበው በላይ ጊዜ ሊወስድ ይችላል፡፡ ስለዚህ ልንጠብቅ የተገባው ጊዜ ይኖራል፡፡ ጥያቄው ትክክለኛውን ወይንም የስህተቱን መንገድ እንጠብቃለን ወይንስ አንጠብቅም ነው? መጥፎውን ከመረጥን ህይወታችን በሰቆቃ ይሞላል፤ የእግዚያብሔርን መንገድ ከመረጥን ግን ታጋሽ እንሆናለን ፣ በምንጠብቅበትም ወቅት ልንደሰት እንችላለን፡፡

ይህ ልምምድን የሚፈልግ ነገር ግን እግዚያብሔር በያንዳንዱ ሁኔታ እንዲረዳን በምንፈቅድ ወቅት ትዕግሰትን የምናዳብርበት ሁኔታ ነው። ይህም የክርስትና አስፈላጊ ልምድ ነው።

ትዕግሰት የመንፈስ ፍሬ ነው፡፡ የሚበለፅገውም በፈተና በመፅናት ነው ስለዚህ ከአዳጋች ጊዜዎች መሸሽና መጥፋት የለብንም፡፡ ምክንያቱም ትዕግሰትን ስናሳድግ መፅሃፍ ቅዱስ እንደሚነግረን ከሆነ እንረካለን ፤ ምንምም አይጎድልብንም፡፡(ያዕቆብ1፡2-4)

ከእግዚያብሔር ጋር ያለን ቁርኝትና ግንኙነት እንኳ ሂደታዊ ለውጥን ያስተናግዳል፡፡ ከምንፈልገው በላይ የሚይስጠብቀን ሁኔታውችን ስናልፍ እሱን ይበልጥ ጥልቅ በሆነ መንገድ ማመን መማር እንጀምራለን፡፡

እመኑኝ ፤ መጠበቁ ከባድ ቢሆንም ፍፁም ጠንካራ ያደርጋችኋል፡፡ በትዕግስት የሚመጣው ጥቅም ከመጠበቅ ጋር ከሚመጣው አለመመቸት የተሻለ ጥቅም ነው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚያብሔር ሆይ ከአንተ ጋር ባለኝ ግንኙነት በጥልቅ ማደግ እሻለሁ ፤ ይህም ታላቅ ትዕግስትን እንደሚሻ አውቃለሁ በዚህም ደግሞ እየበረታሁና እያደኩ እንደምሄድ አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon