በየዕለቱ ለራስ መሞት

በየዕለቱ ለራስ መሞት

በጌታችን በክርስቶስ ኢየሱስ ባለኝ በእናንተ ትምክህት እየማልሁ ፣ ወንደሞች ሆይ ፣ ዕለት ዕለት እሞታሁ፡፡ – 1 ቆሮ 15፡31

ራስ ወዳድነት አብሮን የተወለደ እንጂ የተማርነው ባህሪ አይደለም፡፡ ነገር ግን ጌታን ስንቀበል እና ጌታ በመንፈሳችን ውስጥ ሲኖር ‹‹ለራሳችን መሞትን›› እየተማርን የመንፈስ ቅዱስን ድምጽ እንከተላለን፣ ከዛም ራስ ወዳድነትን እናሸንፈለን፡፡ በእኛ የሚኖረው ታላቁ እርሱ በየቀኑ ራስ ወዳድነትን እንድንገድል ያግዘናል፡፡ ( ገላ 5፡16 )

አሁን ምንም እንኳን ራስ ወዳድነትን ሙሉ በሙሉ ባላሸንፍም ሌሎች ማሸነፋቸውንም እጠራጠራለሁ ፡፡ የታወቀው ታላቁ ክርስቲያን ሐዋሪያው ጳውሎስ ጭምር ከራስ ወዳድነት ጋር ትግል ውስጥ ነበር፡፡ ከራስ ወዳድነት የጸዳ ሕይወት ለእርሱ የሕይወቱ ጉዞው ነበር ፤ በየእለቱ እሞታሁ ብሎ ሲናገር አንብበናል፡፡

እኛም ለዚህ ሕይወት ተጠርተናል ፤ በራስ ወዳድነት እየኖርን ለውጥ እናመጣንለን ብሎ መጠብቅ የማይቻል ነው፡፡ በየዕለቱ ለራሳችን መሞት አለብን፡፡ ይህን ማድረግ ቀላል አይደልም ነገር ግን በእርሱ ላይ ስንደገፍ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ጸጋውን ይሰጠናል፡፡ እውነቱ ብጹ ጽድቅን ፣ ሰላም እና ደስታን በየዕለቱ ለማግኘት ከራስ ወዳድነት የጸዳ ሕይወትን መምራ ነው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

ጌታ ሆ እኔ ፍጹም አይደለሁም ፤ በአንተ ብርታት በየዕለቱ ለራሴ እየሞትኩ መሞት እንደምችል አውቃለሁ፡፡ አንተ በእኔ ውስጥ እንድትኖር ራስ ወዳድነትን እንዴት እደማሸንፍ አሳየኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon