በፍርሃትም ሲጣጣር አጽንቶ ይጸልይ ነበር፤ ወዙም በምድር ላይ እንደሚወርድ እንደ ደም ነጠብጣብ ነበረ። (ሉቃስ 22:44)
ኢየሱስ ወደ መስቀል ሞት ሊወሰድ ሰአቱ ሲደርስ ከስሜቱና ከሃሳቡ ጋር በጥነካሬ ታገለ፡፡ በእግዚአብሔር ፍቃድ ዉስጥ ለማለፍ የእግዚአብሔር ኃይል አስፈልጎት ነበር፡፡ እኛም እንደዚሁ የምናልፍበት ጊዜ አለ፡፡ ጥንካሬ እንዲያገኝ ፀልዮ አገኘ፡፡ መፅሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረዉም ፀለየ መልዓክትም መጥተዉ አገለገሉት፡፡
እግዚአብሔር እንድታደርጉት የሚያዛችሁ ነገር በጣም ከባድ እንደሆነ በፍፁም አትቁጠሩ፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ላመድረግ ፈቃደኞች ስትሆኑና ለዚህም ጉልበት እንዲሰጣችሁ ስትለምኑት እሱም ይረዳችኋል፡፡ ማድረግ ስላልቻላችሁት ነገር ለእግዚአብሔርና ሰዎች በመናገር ጊዜአችሁን አታጥፉ፡፡ ይህን ከማድረግ ይልቅ እግዚአብሔር ኃይል እነዲሰጣችሁ፣ ቆራጦች እንድትሆኑና ጠንካራ እንድትሆኑ ጠይቁ፡፡ እግዚአብሔር አንድን ሰዉ ረድቶ የማይቻለዉን ነገር ችሎከማየትና ምስክር ከመሆን የበለጠ የሚያስደስት ነገር ምንም የለም ብዬ አስባለሁ፡፡
ሰዉ በራሱ ማድረግ የማይችላቸዉ ብዙ ነገሮች አሉ፤ ነገር ግን ከእግዚአብሔር ጋር ሁሉ ይቻላል፡፡ ምናለባትም ኪሳራና ከባድ ነገር በአሁኑ ሰአት ገጥሟችሁ ይሆናል፤ ከሆነም፤ ኢየሱስ በአትክልቱ ቦታ ያሳለፈዉን የትግል ጊዜ ላስታዉሳችሁ እወዳለሁ፡፡ የደም ላብ እሰኪያልበዉ ድረስ በጭነቀት ዉስጥ ገብቶ ነበር፡፡ በእግዚአብሄርኃይል የህንን ጭንቅ ካለፈ፤ እናንተም በእርግጠኝነት ድልን በጸሎትታገኛላችሁ፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ እግዚአብሔር ካቅማችሁ በላይ ሆነን ነገር እንድታደርጉ ፈፅሞ አያደርግም፡፡