“አትረብሹ” የሚለውን ምልክት አውሩዱ

“አትረብሹ” የሚለውን ምልክት አውሩዱ

ቃሉን ስበክ ፣ በጊዜውም አለጊዜውም ጽና ፣ ፈጽመህም እየታገሥህና እያስተማርህ ፣ ዝለፍና ገሥጽ ምከርም፡፡ – 2 ጢሞቲዮስ 4፡2

ለአገልግሎት በምንቀሳቀስባቸው ጊዚያት በብዛት ሆቴሎች ውስጥ እቆያለሁ፡፡ በማረፊያ ክፈሌ ውስጥ ስሆን ማንም እንዳይረብሸኝ ‹‹ አትረብሹኝ›› የሚለውን ምልክት በበራፌ ላይ አስቀምጣለሁ፡፡ በሆቴል ማረፊያ ክፍል በራፍ ላይ ይህን ማድረግ ተቀባይነት አለው፡፡ በሕይወቴ ላይ መለጠፍ አግባብ አይደለም፡፡

በእኛ ጊዜ እና ቀጠሮ ወይም እኛ በሚመቸን መንገድ እግዚአብሔር ስራ እንደማይሰራ አስተውላችሁ ታውቃላችሁ ? ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ እንደ እግዚብሔር አገልጋይ እና እንደ ወንጌል ሰራተኛ የሚጠበቅበትን ድርሻ ቢመችም ባይመችም መወጣት እንዳለበት ያሳስበዋል፡፡ ጢሞቲዎስ እንደኛ በምቾት የተጠለፈ ሰው መሆኑን እጠራጠራለሁ፡፡ ነገር ግን እርሱ ይህን መስማት ካለበት እኛ ደግሞ አብልጠን ልንሰማው ይገባናል፡፡

የእግዚዘብሔር ጥሪ ምቾች የለውም ብለን በልባችን በራፍ ላይ የ‹‹አትረብሹኝ›› ምልክት ማድረግ በጣም ቀላል ነው ይሁን እንጂ ታላላቅ እድሎችን ማጣታችንን ግን ግልጽ ነው፡፡ ይህን ልብ አድርጉ ምንም ነገር እንድናደረግ እግዚአብሔር ሲጠይቀን በምናልፈበት መንገድ ውስጥ ያለው ምቾት ማጣት እና ተግዳሮት የሚገባ መሆኑን እወቁ፡፡ እርሱን ስንታዘዘ ፈቃዱን እድናከናውን መንገዳችንን ቀና ያደርግልናል፡፡

ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ዛሬ በልቤ በራፍ ላይ የሰቀልኩት ‹‹አትረብሹኝ›› የሚለውን ምልክት ማውረድ እፈልጋለሁ፡፡ ምቾት ባይሰማኝም እንኳ አንተን ለመታዘዝ እና እንዳደር የፈለከውን ለማድረግ እፈልጋለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon