አትጨነቁ…አምልኩ!

አትጨነቁ…አምልኩ!

አንድ ጠዋት ልጸልይ ተቀምጬ በጸሎት ፋንታ ስላለሁበት ሁኔታ መጨነቅ እና ምን ማድረግ አለብኝ ብዬ ማሰብ መጀመሬን አስታውሳለሁ፡፡

ድንገት በመንፈሴ ውስጥ ረጋ ያለ ትንሽ ድምጽ ጆይስ ችግርሽን ነው ወይስ እኔን ነው ልታመልኪ ያሰብሽው? አለኝ፡፡አያችሁ ችግሬን ብረሳውና እርሱን በማምለክ ጊዜዬን ባሳልፍ እግዚአብሔር ችግሮቼን ለመፍታት ከፈቃደኛነት በላይ ነበር፡፡

ጌታን ስናመልክ የተጫነንን ስሜታዊ እና የሀሳብ ጫና እናራግፋለን፡፡በእግዚአብሔር ድንቅነት ውስጥ ይዋጣል፡፡አይኖቻችንን በእርሱ ላይ አድርገን ስናመልከው ለህይወታችን ያለውን እቅዱን ሁሌም ለእኛ ጥቅም ሲሰራ እናያለን፡፡

መጽሀፍ ቅዱ ሲናገር ጌታን በአምላካዊ ፍርሀት በእውነት የሚያመልኩት አንዳች አያጡም፡፡የሚያስፈልጋችሁ ነገር ሁሉ እንደሚሟላ እርግጠኛ መሆን ትፈልጋላችሁ?ስለዚህ መጨነቅ ሳይሆን ማምለክ እንዳለባችሁ አስታውሱ፡፡

እያጋጠሟችሁ ያሉት ነገሮች ምንም ከባድ ቢሆኑም እግዚአብሔርን ማመስገን እና ክብርን በመስጠት ቀጥሉ፡፡እምነት በልባችሁ ይነሳና ታሸንፋላችሁ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ አልጨነቅም፡፡ይልቁንስ ማምለክን እመርጣለሁ፡፡አንተ ታላቅ እና ሀይለኛ ነህ፣እናም ለእኔ ካለህ መልካምነት እና ፍቅር የተነሳ የሚያስፈልጉኝ ነገሮች ሁሉ እንደሚሟሉ አውቃለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon