
እርሱ ብቻ ልባቸውን ሰራ ስራቸውንም የሚያስተውል፡፡ መዝ 33÷15
መዝሙረ ዳዊት 33÷15 ስለ እኛ ስለግላችን ይናገራል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር እያንዳንዳችን በግላችን ልባችንን ያድሳል (ይቀድሳል) የእኛ ፀሎት በተፈጥሮ የሚፈሰውና ሃሣብ የሚነሣው ከልብ ስለሆነና እንዲህም አድርጎ ስለፈጠረን ወይም ስላበጀን ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ያለንን የግንኙነት መንገዳችንን ባሳደግን መጠን ከእኛ የበለጠ ልምድ ካላቸው ሰዎች እንማራለለን፡፡ ነገር ግን መጠንቀቅ ያለብን የእነርሱን ሕይወት እንዳንኮርጅና የሕይወት መመሪችን መለኪያ እንዲሆኑልን መፍቀድ የለብንም፡፡ የብዙዎችን ሰዎች ምሳሌ መውሰድና ምሳሌ መሆን ጥሩ ቢሆንም ኢየሱስ ግን የሕይወታችን የመለኪያ ቱንብ እንዲሆንልን ተስፋ አደርጋለሁ፡፡ በአንተ የግል ፀሎት ላይ ሌላ ሰው ገብቶ ከአንተ ጋር እንድተባበር የእግዚብሔር መንፈስ ምርት እስከሆነ ድረስ ምንም ስህተት የለውም፡፡ ነገር ግን ስህተቱ ሌሎች የሚደርጉትን አንተም እንድታደርግ ውስጥህ መረጋጋትና ሠላም የማይሰጥህን የሚስገድድህ ከሆነ ነው፡፡
እኔ የማበረታታህ የራስህ የሆነ ከእግዚአብሔር ጋር የምትነጋገርበትና እርሱን ድምፅ የምትሰማበትን መንገድ /ዘዴ/ እንድትዳብር ነው፡፡ ከሌሎች ጋር ለመወዳደር ወይም የፀሎታቸውን ዘዴ አትኮርጅ፡፡ እንዲሁም የተማርካቸውን የፀሎት መመሪያዎችን ለመፈፀም እራስህን አታስገድድ፡፡ እግዚአብሔር አንተን ያበጀበት በእራሱ መንገድ አንተ እንድትሆን የፈለገውን በማስታወስ እራስህን ሁን፡፡ እርሱ አንተ በሆንከውና በአንተ በማንነትህ ደስተኛ በመሆን ልዩ በሆነ መንገድና በራስህ መንገድ ይነግርሃል፡፡
የዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔር በማንነትህ እንዳለህ ይወድሃል፡፡ እንዲሁም አነጋገርህን ይወዳል፡፡ ከእርሱ ጋር ባለህ ነገር በማንነትህ አትሸማቀቅ፡፡