አንተ ደክመሃል ወይስ ኢየሱስ ከብሯል

አንተ ደክመሃል ወይስ ኢየሱስ ከብሯል

አሁን ግን ለእርሱ ለታሰርንበት ስለ ሞትን፥ ከሕግ ተፈትተናል፥ ስለዚህም በአዲሱ በመንፈስ ኑሮ እንገዛለን እንጂ በአሮጌው በፊደል ኑሮ አይደለም። – ሮሜ 7፡6

እኔ እንደማምነዉ ብዙ ሰዎች የሚጨነቁበትና ሸክም የሚያበዙበት ዋናዉ ምክንያት የእግዚአብሔርን ሳይሆን የራሳቸዉን ዕቅድ ስለሚከተሉ ነዉ፡፡

በማንኛዉም ነገር ላይ ስንሳተፍ ጉልበታችንን የት ማፍሰስ እንዳለብን የመንፈስ ቅዱስ ምሪት ያስፈልገናል፡፡  እርሱ እሺ ሲል እሺ እርሱ እምቢ ሲል እምቢ ማለትን መማር አለብን፡፡ ለእግዚአብሔር ምሪት ታዛዦች ስንሆን እርሱ የሰጠንን ነገር ለማጠናቀቅና በሰላም ለመጓዝ እንበቃለን፡፡

ሮሜ 7፡6 የሚለዉ በመንፈስ ኑሮ እንድንመራ ነዉ፡፡ ብዙ ጊዜ ሲደክመኝ መንፈስ ቅዱስ እረፊ ሲለኝ እኔ ግን ወደ ጉዳዮቼ የሄድኩባቸዉን ጊዜያት አስታዉሳለሁ፡፡  በመጨረሻም በድካም ብቻ ሳይሆን እጅግ በስልችት ጨርሻለሁ፡፡ እንደምታዉቁት ብዙ የሚደክሙ ሰዎች ነጭናጫና ትዕግስተ አልባ ናቸዉ፡፡

መንፈስ ቅዱስን ስንታዘዝ ኢየሱስ ይከበራል፡፡ ስለዚህ እንዲህ ልጠይቃችሁ “እናንተ እየደከማችሁ ነዉ ወይስ ኢየሱስ እየከበረ ነዉ?” መንፈሱን ተከተሉ እርሱን በህይወታችሁ አክብሩ፡፡


የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ! ፈቃድህን ለመታዘዝ እጅግ መድከም አልፈልግም፤ የአንተን ዕቅድ ለመከተልና በህይወቴ ላልቅህ መርጬአለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon