ዕረፍ፣ እኔም አምላክ እንደ ሆንሁ እወቁ፡፡ መዝ 46÷10
በሕይወቴ መናገር በቀላሉ ስለሚቀናኝ፣ ለመስማት ወይም ለማዳመጥ መማር ነበረብኝ፡፡ አንድ ወቅት ከባለቤቴ ጋር ቁጭ ብለን እንድናወራ ፈለኩና ስጠይቀው ሲመልስልኝ ጆይስ አይደለም አንቺ አውሪ እኔ አዳምጥሻለሁ እንጅ ሁለታችን አናወራም አለኝ፡፡ እርሱ ትክክል ነበር፤ አብረን ለመነጋገር ከተፈለገ ተራ በተራ በመነጋገርና በመደማመጥ እንድንግባባ እኔ መለወጥና አድማጭ መሆን አለብኝ ነበር፡፡
ነገሩን ሳይ ልክ ባለቤቴ ዳዊትን በሚቀርብበት መንገድ እግዚአብሔርን እንደሚያቀርብ ተረዳሁ፡፡ በእግዚብሔር ቤት እናገር እናገርና እንዲነገረኝ ሳዳምጠው ስለማያናግረኝ ከእግዚአብሔር አልሰማውም ወይም አልተናገረኝም በማለት አስባለሁ፡፡ እውነታው ሲታይ ግን እኔው እራሴ ጊዜ ሰጥቼው አላደመጥኩም፡፡ የዛሬ ጥቅስ የሚያስተምረን እንድናርፍ እና እግዚአብሔር እግዚአብሔር እንደሆነ ማወቅ ነው፡፡ ለብዙዎቻችን ማረፍ በጣም ከባድ ነገር ይሆንብናል፡፡ ምክንያቱም ሥጋችን በተለያዩ ነገሮቻችን ቀልጣፋና የባከንን እንድንሆን ስለምንፈልግ ነው፡፡ ነገር ግን የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት ከፈለግን በእግዚአብሔር ፊት ጊዜ ልንወስድና እርሱን ለመስማት የግድ መማር አለብን፡፡ ለብዙ ሰዎች ማድመጥን መማር መለማመድ የግድ የሚስፈልገን ጉዳይ ነው፡፡
አንዳንድ ጊዜ ይህ ማለት ፀጥና ዝግ ብሎ ያለምንም ንግግር በእግዚአብሔር መገኘት ውስጥ መቆየትን የሚጠይቅ ይሆናል፡፡ ማድመጥን መለማመድ የግድ አለብን፡፡ አንደኛው መንገድ እግዚአብሔርን አንድን ሰው እንድታበረታታው ወይም እንድትባረክ እንዲሰጥ ማድረግ ከዚያ ዝግ ብሎ በፊቱ ፀጥ ማለት፡፡ ከዚያ በኋላ ወዲያው ስለ አንድ ሰው በልብህ በማምጣት መናገር ይጀምራል፡፡ ምናልባት ስለዚህ ጥልቅ የሆኑ ነገሮች ስለ እነርሱ ለማበረታት ያመጣል፡፡ ለእግዚአብሔር መመርያ ባዳመጠን ልክ ገንቢ ሃሣቦችን ወደ እኛ ያመጣል፡፡ ጊዜ ውሰድና በፀጥታ ከእግዚአብሔር ጋር በመሆን በጥንቃቄ እርሱን ሰማ እርሱ የሚያሳየን ማድረግ የሚገባህን ከእርሱ መመሪያ ተቀበል፡፡
የዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ዛሬ ጊዜ ወስደህ በፀጥታ አድምጥ፡፡