“እውነት እላችኋለሁ፣ ካልተለወጣችሁ እንደ ሕፃናትም ካልሆናችሁ ፈጽሞ ወደ መንግሥተ ሰማይ አትገቡም። (ማቴዎስ 18: 3)
የዛሬው ጥቅስ ልጆችን የሚታመኑ፣ ዝቅ ያሉ፣ አፍቃሪ እና ይቅር ባይ እንደሆኑ ይገልጻል። በእነዚህ አራት ባህሪያት ብንኖር በሕይወታችን ከእግዚአብሔር ደግሞም ከሌሎች ሰዎች ጋር ባለን ግንኙነት ምን ያህል እንደምንደሰት አስብ። በግልጽ ለማየት እንደሚቻለው፣ ኢየሱስ እነዚህ ባሕርያት እጅግ አስፈላጊ እንደሆኑ ያስባል፣ ምክንያቱም ያለእነሱ ወደ መንግስተ ሰማያት መግባት እንደማንችል ተናግሯል። የእግዚአብሔርን መንግሥት ጥቅሞች ማጣጣም እና በተመሳሳይ ጊዜ መጥፎ አመለካከቶችን ይዘን መቆየት አንችልም።
የእግዚአብሔርን ድምፅ ስለ መስማት ሳስብ እንደ ልጅ መሆን ማለት በጣም አስፈላጊ ነገር እንደሆነ አያለሁ ምክንያቱም ልጆች የሚነገራቸውን ያምናሉ። አንዳንድ ሰዎች ልጆች ሞኞች ናቸው ይላሉ፣ ምንም ያህል አስቂኝ ቢመስልም ማንኛውንም ነገር ያምናሉ። ግን ልጆች ሞኞች አይመስሉኝም፤ እነርሱ የሚያምኑ ይመስሉኛል። በእርግጥ እግዚአብሔር ሞኞች ወይም ቂሎች እንድንሆን አይፈልግም፤ እኛ የምናምን እንድንሆን ይፈልጋል። አንዳንድ ጊዜ በምንወዳቸው እና በምናምናቸው ሰዎች እንከዳለን እናም በዚያን ጊዜ ሁሉንም ለማመን እንፈተናለን፣ ግን አንድ ሰው ላደረገብን ነገር ሁሉም እንዲከፍል ማድረግ አንችልም።
በዓለም ላይ እምነት ሊጣልባቸው የማይችሉ ሰዎች አሉ፣ ግን ደግሞ ብዙ ጥሩ ሰዎችም አሉ ስለዚህ በጥርጣሬ መንፈስ ለመኖር እምቢ ማለት አለብን።
እግዚአብሔር ሙሉ እምነት የሚጣልበት ነው። ሁሉም የሰው ልጆች፣ በሚያሳዝን ሁኔታ ያለምንም ቅድመ ሁኔታ ሊታመኑ አይችሉም፣ ግን እግዚአብሔር ይችላል።
ፍፁም እምነት የሚጣልበት ስለሆነ በፍፁም እርሱን እና የሚልህን ሁሉ በማመን እግዚአብሔር እንደ ልጅ ወደ እርሱ እንድትመጣ ይፈልጋል።
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ አንድ ወይም ሁለት መጥፎ ልምምዶች መላ ሕይወትህን እንዲገዙ አትፍቀድ።