እግዚአብሔር ሁልጊዜም ከኛ ጋር ነዉ

ለዓለምና ለዘላለም ይህ አምላካችን ነው፥ እርሱም ለዘላለም ይመራናል። (መዝ 48:14)

በምድር ላይ ባለን የህይወት እድሜ ሁሉ እግዚአብሔር ከኛጋር እንደሆነ ማመን የሚያጽናና ነገር ነዉ፡፡ እሱ ሁልጊዜ ከኛ ጋር ስለሆነ ፈጽሞ ብቻችንን አንሆንም፡፡ እሱ ሁልጊዜ ይጠብቀናል፡፡

እግዚአብሔርን የመስማት ልምምዳችሁን ስታሳድጉ፣ እሱ ከሚናገርባቸዉ መንገዶች አንዱ መለኮታዊ ምሪት እንደሆነ ልታዉቁ ይገባል፡፡በምታደርጉት ሁሉ ለእግዚአብሔር እዉቅና የመስጠትን መንፈሳዊ ልምምድ አድርጉ፣ ምሪትን መጠየቅና በእምነት ደግሞ መቀበልን መለማመድ፡፡

እኔ ዛሬ ወደ ገበያ እሄዳለሁ ለዚህም ምሪትን ከእግዚአብሔር እጠይቃለሁ፡፡ ወዳላሰብኩት ነጋዴ እንድሄድ ሊያደርግ ይችላል፣ ወይም ስመለስ መጽናናት የሚያስፈልገዉን ሰዉ እንዳገኝ ሊያደርግ ይችላል፡፡ እያንዳንዱ እርምጃዎቼ በእግዚአብሔር ፈቃድ ስር እንዳለ አምናለሁ (መዝ 37:23ን ተመልከቱ) ፡፡ እግዚአብሔር መግዛት በሚያስፈልገኝና በማያስፈልገኝ ነገር ሁሉ እንደሚረዳኝ አምናለሁ፡፡ በሁሉ ነገር እሱን አስቀድማለሁ፡፡ እናንተም እንደዚሁ እንደምታደርጉ አምናለሁ፡፡

በማስተማር አገልግሎቴ፣ አብዛኛዉን ጊዜ መለኮታዊ ምሪትን ተለማምጃለሁ፡፡ ማለት ያለብኝንና የማምነበትን ነገር እለማመዳለሁ፣ ይሁን እንጂ አብዛኛዉን ጊዜ እኔ ባቀድኩት መንገድ ሳይሆን በሌላ መንገድ እግዚአበሔር ሲመራኝ አያለሁ፡፡ የማስተምራቸዉ ሰዎች ምን መማር እንዳለባቸዉ እሱ ያዉቃል እሱ እንዲመራኝ ማድረግ የኔ ስራ ነዉ፡፡

እግዚአብሔርን መስማት የሚለመድ ነገር መሆኑን እንድታስታዉሱ አበረታታችኋለሁ፡፡ ታምራዊ የሆነ ልምምድ ለማድረግ አትታገሉ፣ ከዚህ ይልቅ የእግዚአብሔርን መለኮታዊ ምሪት ፈልጉ፡፡ መንፈሱ በዉስጣችሁ ስለሆነ በምታደርጉት ሁሉ እሱን እንድታሳትፉ ይፈልጋል፡፡ ዛሬ በምታደርጉት ወይም መሄድ ወደምትፈልጉት ሁሉ፣ እሱ እነዲመራችሁ እሹ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜ ከናንተ ጋር ነዉ በምታደርጉት ነገርም ሁሉ ዛሬ ይመራችኋል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon