እግዚአብሔር በጥበብ ይናገርሃል

እግዚአብሔር በጥበብ ይናገርሃል

ረቂቅ እውቀትን ብትጠራት ለማስተዋልም ድምፅህን ብታነሳ እርሷንም እንደ ብር ብትፈልጋት እርሷንም እንደተቀበረ ገንዘብ ብትሻት፣ የዚያን ጊዜ እግዚአብሔርን መፍራት ታውቃለህ፣ የአምላክህን እውቀት ታገኛለህ፡፡ ምሣ 2÷3-5

የዛሬ ጥቅስ የሚያነሳሳን ጥበብን እንድንሻና ለማስተዋልም እንድንጮህ ነው፡፡ ምክንያቱም የእግዚአብሔር ጥበብ ከሰው ልጆች ጥልቅ ሃሣብ በጣም የላቀ ስለሆነ ነው፡፡ እግዚአብሔር ነገሮችን ከጅማሬው መጨረስን ያያል፡፡ እርሱ የሰዎችን የልብ ሃሣብና ዝንባሌ ያያል፡፡ እርሱ የማናውቀውን ነገሮች እርሱ ያውቃል፡፡ በሕይወታችን በጠላት ጥቃት ስር በመሆን በሙሉ ጭቅጭቅና ወከባ ውስጥ እራሳችንን ልናገኝ እንችላለን፡፡ የእግዚአብሔር ጥበብ ግን ልዩነት ያደርጋል፡፡ ይህ ጥበብ ደግሞ የምገኘው እርሱን በመጠቅ ብቻ ነው፡፡

ብዙውን ጊዜ እግዚአብሔር ለእኛ ሲነገረን ጥበብን ያፈጠቃል፡፡ በሁኔታዎች ላይ የመረዳት ዕይታን በመካፈል ወይም ደግሞ ውሳኔን ስንወስን ምን ማድረግ እንዳለብን ይነግረናል፡፡ ጥበብ እንዲታወቅ በተለያዩ መንገዶች እንዲታወቅ ያደርጋል፡፡ እኛም ይህንን ሁልጊዜ እንደውድ የሥጦታ እቃ መቀበል አለብን፡፡

እኔ የማበረታታህ ለእግዚአብሔር ጥበብ ዋጋ ልትሰጠውና እንደመንፈሳዊ ውድ ሃብት እንደሆነና ያለ እርሱ ምንም ማድረግ እንደማትችል ማሰብ አለብህ፡፡ ምክንያቱም ያለ እርሱ የተሳካ ሕይወት መኖር ስለማትችል ነው፡፡ የፀሎት ልምድህ የእግዚአብሔርን ጥበብ በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ እንዲሰጥህ ፀልይ ለብዙም ሆነ ለጥቂቱ፡፡ እርሱም ይሰጥሃል አንተም በውጤቱ ደስተኛ ትሆናለህ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ምንም ጥቂት ነው የሚል የእግዚአብሔርን ጥበብ የማያስፈልግ ነገር የለም፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon