ከጌታ ኢየሱስ ጸሎት መማር

ከጌታ ኢየሱስ ጸሎት መማር

አባት ሆይ፥ የሚያደርጉትን አያውቁምና ይቅር በላቸው አለ። (ሉቃስ 23:34)

ሰዎች የሚጸልዩበት መንገድና የሚጸልዩባቸዉ ጉዳዮች ብዙ የሆነ የራሳቸዉን ባህሪና መንፈሳዊ ማንነት እንደሚያሳዩ አምናለሁ፡፡የጸሎት ህይወቴ መንፈሳዊ ብስለት የሌለዉ ጊዜ እንደነበረአስታዉሳለሁ፡፡ ዳግም የተወለድኩ እንኳ ብሆንም፣ መንፈስ ቅዱስን ተሞልቼ የእግዚአብሔርን ቃል ባስተምርም፣ ጸሎቶቼ በስጋ ሀሳብ የተሞሉ ነበር፡፡ ስጸልይ የጸሎት ርእሶች በዝርዝር ነበሩኝ፡፡ እግዚአበሔርም
ሁሉንም እሺ የሚል ይመስለኝ ነበር፡፡ አብዛኛዎቹ ስለምድራዊ ጉዳዮች ነበሩ፡-“ጌታሆይ አገልግሎቴን አሳድገዉ፤ አዲስ መኪና ስጠን፤ ይሄን አድርግ፤ ያንን አድርግ፡፡ ዳዊትን ለዉጥ፡፡ የልጆቹን ባህሪ ለዉጥ፣” እናም ወዘተ፡፡

ለዚህም እግዚአብሔር እንደዚህ በቀላሉ መልስ ሰጠኝ፣ “የኢየሱስንና የጳዉሎስ ጸሎቶችን እድትመረምራቸዉ እፈልጋለሁ፡፡ ከዚያ በኋላ ስለ ጸሎት ህይወትህ እናወራለን፡፡” በርግጥም በመጽሀፍ ቅዱስ ዉስጥ የተጸለዩ ጸሎቶች፣ በተለይም በመዝሙረ-ዳዊት ዉስጥ አሉ፣ ነገር ግን እግዚአብሔር በወንጌላት ዉስጥ ያሉትን የኢየሱስን ጸሎቶች፣ በመልክቶቹ ዉስጥ ያሉትን የጳዉሎስ ጸሎቶችእንድጸልይ ነገረኝ፡፡

ኢየሱስ በጸለየበት መንገድ መጸለይ ስጀምር፣ የእግዚአብሔርን ቃል መሰረት አድርጎ ከመጸለይ የተሻለ ሀይል ያለዉ ጸሎት እንደሌለ ተረዳሁ፡፡ ምክንያቱም በእግዚአበሔር ዘንድ አስፈላጊ የሆነዉን ነገር
ያሳየናል፡፡ እሱ ከላይ ባየነዉ ክፍል ያየነዉ አይነት ጸሎትና የሚከተሉትን ብዙ ጸሎቶች ጸለየ “ቀድሳቸዉ (አንጻቸዉ)፣ ለራስህ ለያቸዉ፣ ቅዱስ አድርጋቸዉ] በእዉነት ፤ ቃልህ እዉነት ነዉ” (ዮሐ
17:17) ፤ በህዝቦቹ መካከል አንድነት እንዲኖር (ዮሐ 17:23 ተመልከቱ) ፤ ለጴጥሮስም በጸለየዉ ጸሎት “በተለይም፣ እምነትህ እንዳይጠፋላንተ ለመንኩ፤[ጴጥሮስ]” (ሉቃ 22:32)

እኔ ወንጌላትን እነድታነቡና ጌታ አየሱስ የጸለያቸዉን ጸሎቶች ልብ እንድትሏቸዉ፣ ከዚያም በተመሳሳይ መንገድ ስትናገሩ እግዚአብሔርን እንድትሰሙ አበረታታችኋለሁ፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡ እግዚአብሔር ለእናንተ ያለዉን ፍቅር እዲገልጥላችሁ፣ እሱንም እንደትረዱ ጸልዩ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon