ወደ እግዚአብሔር መገኘት በምሥጋና ግባ

ወደ ደጆቹ በመገዛት ወደ አደባባዮቹም በምሥጋና ግቡ፡፡ መዝ፡ 100 4

ከእግዚአብሔር ለመስማት ከሚቀርብበት መንገዶች ውስጥ አንዱ፡- በአክብሮት፣ ከተሰበረ ልብ በሚቀርብ ምሥጋናና አምልኮ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሚደሰተው መገኘቱንና ኃይሉን በእውነት እርሱን ለሚያከብሩትና ለሚያመልት በማሳወቅ ነው፡፡ የእርሱ መገኘትና ኃይል ሲመጣ፡- የእርሱን ድምፅ እንሰማለን፣ ተዓምራቶችን እናያለን፣ ሰዎች ይፈወሳሉ፣ የሕይወት ለውጥ ይመጣል፣ መነቃቃትና ለውጥ ከውስጥ ወደ ውጭ ይሆናል፡፡

ከምትፈልጋቸው ነገሮች መካከል አንዱ ከእግዚአብሔር ጋር ኅብርት መፍጠር አይደለምን; ለእርሱ ስትናገርና የእርሱን ድምፅ ስታዳምጥ በቅድሚያ ትፀልይ የለምን; ምክንያቱም የተወሰነ ለውጥ ወይም መሻሻል በተወሰነ የሕይወት ጉዳይ ትፈልጋለህ፡፡ አዲስ ሥራ እንዲሰጥህ ብትጠይቅ ያም ለውጥ ነው፡፡ አንድ የምትወደው ሰው ወደ ጌታ እንዲመጣ ከፀለይክለት ያም ለውጥ ነው፡፡ ጌታ የበለጠ እራሱን እንዲገልፅልህ ብትጠይቅና በመንፈሣዊ ሕይወትህ ሕይወትህ እንድታድግ ብትፀልይ ያም ለውጥ ነው፡፡

ለጎዳና ተዳዳሪ ወጣቶች ሃሽሽ መጠቀም እንዲያቆም ብትፀልይ ያም ለውጥ ነው፡፡ በቀላሉ ቶሎ ብለህ ቁጡና ግንፍልተኛ እንዳትሆን ብትፀልይ ያም ለውጥ ነው፡፡ ለምንም ነገር ስትፀልይ አንዱ መንገድ በምሥጋናና በአምልኮ ስሆን በጣም ጥሩ ነው፡፡ እነዚህ ልብህን በትክክለኛ መንገድ በእግዚአብሔር ሬት እንድታደርግና የእርሱን ድምፅ ለመስማትና ለውጥ እንዲመጣ ያደርጋል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት ስትፈልግ በምሥጋና በአምልኮ ቅረብ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon