የሕይወት አጋዥ

የሕይወት አጋዥ

አቤቱ የሰው መንገድ ከራሱ እንዳደለ አውቃለሁ አካሄዱንም ለማቅናት ከሚራመድ ሰው አይደለም፡፡ ኤር 10 23

ኤርሚያስ በዛሬ ጥቅስ ውስጥ አንድ እውነታ ይናገራል፡፡ በእርግጥ በእኛ ለሰው ልጆች ሕይወታችንን በሥርዓት ለማምራት ያስቸግራል፡፡ ለእኛ እና ለእናንተ እርዳታ ያስፈልገናል ደግሞ በብዙ ያስፈልገናል፡፡

ይህንን ማመን ደግሞ የመንፈሳዊ እውነታ መረዳት ብስለት እንጂ የደካማነት ምልክት አይደለም፡፡ በእግዚአብሔር ውስጥ ያለውን ብርታት ካልፈለግን ደካማነታችን ፈጥኖ በሕይወታችን ይገለጣል ደግሞም በኑሮአችን ይታያል፡፡

ምናልባት አንተ በብዙ ጥረት ነገሮችን ለማስተካከል እየሠራ ሳለህ ሁልጊዜ ነገሮችን የማይሳኩለት ሰው ትሆን ይሆናል፡፡ የአንተ ችግር አለመሳካቱ ሳይሆን ወደምረዳህ ምንጭ በቀላሉ አለመሄድህ ነው፡፡ እግዚአብሔር ያለ እርሱ እውነት ስኬት እንድናገኝ አይፈቅድም፡፡ እውነተኛ ስኬት ስኬት ዝም ብሎ በነገሮች መሰብሰብ ላይ የተመሠረተ መበልፀግ እንዳለሆነ አስታወሰ፡፡ እግዚአብሔር በሚያደርግልን አቅራቦት በእውነተኛ ደስታ በሕይወትና በነገሮች የመኖር ችሎታ ነው፡፡ ብዙ ሰዎች ስልጣን፣ ገንዘብ፣ ኃይል፣ ዝና፣ እና ሌሎችም ይህን የመሳሰሉ ነገሮች አሉአቸው፡፡ ነገር ግን ምናልባትም ደግሞ በጣም ወሳኝ ነገሩን ጥሩ ግንኙነት ትክክለኛ አቋም፣ ከእግዚአብሔር ጋር ሠላም፣ ደስታ፣ እርካታ፣ ጤንነት፣ ሕይወትን የመጣጣም ችሎታ ላይኖረው ይችላል፡፡

በመዝሙር 127 1 እንደተገለፀው እግዚአብሔር ቤትን ካልሰራ ሠራተኛ በከንቱ ይደክማል ይላል፡፡ እኛ ልንገነባ እንችል ይሆናል፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ከሌለበት ግንባታው ላይከርም ይችላል፡፡ እርሱ የሕይወታችን አጋዥ ነው፡፡ እንደዚያውም በሕይወታችን በምናደርገው ነገር ሁሉ መካፈል ይፈልጋል፡፡ ይህንን እውነት ማመን ከእርሱ ጋር ጉዞ ለመጀመር አስደሳች የሕይወት ጅምር ነው፡፡

ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- እግዚአብሔርን የሕይወትህ አጋዥ አድርግ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon