መልካም፣ደስ የሚያሰኝና ፍጹም የሆነውን የእግዚአብሔር ፈቃድ ምን እንደሆነ ፈትናችሁ ታውቁ ዘንድ በአእምሯችሁ መታደስ ተለወጡ እንጂ ይሄንን አለም አትምሰሉ፡፡ – ሮሜ 12፡2
“አዕምሮና ማባከን እጅግ መጥፎ ነገር ነው” የሚለውን አባባል ሰምታችሁ ታውቃላችሁ? አዕምሯችን ለመልካም ነገር ፣ለመማር፣ለመፍጠር፣ለማሰብ፣ለማደግ ብዙ አቅም አለው፡፡አቅሙን አሟጠን መጠቀም ሲያቅተን የሚያሳዝን ነገር ነው፡፡
በህይወቴ ብዙ አሉታዊ፣የሚያሰቃዩ፣የጥፋተኘነት፣ይቅር ያለማለት፣አሳፋሪ እና ከሳሽ የሆኑ ጎጂ ሀሳቦች ወደ አዕምሮዬ እንዲገቡ የፈቀድኩበት ዘመን ነበር፡፡ችግሩ የማስበውን መቆጣጠር ወይም ማተኮር እና ማመን ያለብኝን ሀሳብ መምረጥ እንደምችል አለማወቄ ላይ ነበር፡፡
እውነት ያልሆነ ነገር እያሰብኩ ከሆነ ማሰቤን ለማቆም አቅሙ እንዳለኝ አልተረዳሁም ነበር፡፡ስለምን ማሰብ እንዳለብኝ መምረጥ እንደምችል ማንም ነግሮኝ አያውቅም ነበር፡፡ነግሯችሁ የሚያውቅ ሰው አለ? ከሌለ እኔ ዛሬ እዚህ ያለሁት ሀሳባችሁ እንዲቆጣጠራችሁ መፍቀድ እንደሌለባችሁ ልነግራችሁ ነው፡፡የእግዚአብሔርን ሀሳብ ለማሰብ እና በሱ ላይ ለማተኮር መምረጥ ትችላላችሁ!
ሮሜ 12፡2 በአዕምሯቸሁ መታደስ ተለወጡ… ይላል፡፡ እግዚአብሔር በአዕምሯችሁ ውስጥ ያለውን ጦርነት እንድታሸንፉ ሊረዳችሁ ይፈልጋል፡፡ይሄ ግን በተግባራዊ መልኩ ምን ይመስላል?
ይሄ ለእኔ በጣም ብዙ ጊዜ የሰራልኝ እና ለእናንተም እንደሚሰራላችሁ የማውቀው ነገር ነው፡በሚቀጥለው ጊዜ በአዕምሯችሁ ውስጥ ትግል ሲነሳ ትታችሁት እግዚአብሔርን የምታመሰግኑበት አንድ ምክንያት እንድትፈልጉ እፈልጋለሁ፡፡ስለመልካምነቱ እና ህይወታችሁን ስለባረከበት በረከቶች አመስግኑት፡፡ይሄንን በትጋት ማድረጋችሁን ስትቀጥሉ ህይወታችሁ መቀየር ሲጀምርና ነገሮች እየተሻሻሉ ሲሄዱ ታያላችሁ፡፡
እግዚአብሔር የሰጣችሁን ሀይል አውቃችሁ በየቀኑ በአስተሳሰባችሁ በፍቅሩ ሙላት ትጓዙ ዘንድ ጸሎቴ እና ተስፋዬ ነው፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
በአስተሳሰቤ ሀይልህን መለማመድ እፈልጋለሁ፡፡በመልካምነትህ እና ለእኔ ባለህ ፍቅር ላይ ማተኮር እፈልጋለሁ፡፡በመንገዴ ምንም አይነት አሉታዊ ሀሳብ ቢመጣ አንተ ከሁሉ በላይ እንደሆንህ እና ከሁሉ እንደምትሻል አውቃለሁ፡፡