
ትዕግስትም ምንም የሚጎድላችሁ ሳይኖር ፍጹማንና ምሁራን ትሆኑ ዘንድ ሥራውን ይፈጽም፡፡ ያዕ 1÷4
የዛሬው ጥቅስ ስለ ጽናት ይነገራል፡፡ ለመጽናት መረጋጋት ያስፈልጋል፡፡ የሚፀና ሰው አይነቃነቅም የተረጋጋ የፈለገ ነገር ቢሆን ለቁጣ የዘገየ ነው፡፡ የጸና አማኝ ለሰይጣን ምላሽ ወገብና ጅማት ይበጥሳል፡፡ በመንፈሳዊ ሕይወታችን ማደግና መለወጥ በማሳየት ወደ ጽናት መድረሳችን የሚታወቀው ሰይጣን ወይም ጠላት ወደ እኛ የምልከውን ትናንሽ ጉዮች ጋር መነዛነዝና መጨቃጨቅ ውስጥ ከመግባት በመራቅ ነው፡፡ ከመንገዳችን ስተን እንድንወጣ ወይም እንድንለቅ የሚያደርገው ጥረት እኛን ማስገረም ወይም ልንፈራም አይገባም፡፡ እኛ ስንፀና በቀላሉ ተስፋ አንቆርጥም የጀመርነውን አናቆምም ሥፍራችንን አንለቅም፡፡
ለመጽናትና ላመነቃነቅ እግዚአብሔርን ማወቅ እርሱን ማወቅና መወዳጀት በጣም የሚያስፈልግ ነው፡፡ በሕይወታችን ጉዞአችን አውሎ ነፋስ ተነስቶ አካባቢያችን ሲያናውጥ የእርሱን ድምፅ መስማት አለብን፡፡ እንዲሁም ደግሞ አሸናፊውን ኃይል በኢየሱ ስምና በደሙ ውስጥ ያለውን መብታችን በደንብ ማወቅ አለብን፡፡ ደግሞ ‹‹ይህም ደግሞ እንደሚያልፍ ‹‹በማስታወስ እርግጠኛ በሆነው ድላችን ላይ አይናችንን ማኖር አለብን፡፡ አለበለዚያ ግን እራሳችንን ጠላት ወደ እኛ ለሚወረውረው ጥቃት በማጋለጥ ወደ እኛ በሚወረውረው ነገሮች እንጨናነቃለን፡፡ እኛ በጽናት በመቆም ስንቀጥል እግዚአብሔርም ደግሞ ኃይሉን በሕይወታችን ይለቃል፡፡ ዛሬ ምንም ዓይነት ነገር ቢያጋጥምህም እግዚአብሔር ከአንተ የምፈልገውን ሥራ በትዕግስት አከናውን፡፡
ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- የሰይጣንን በማርበድበድና በእግዚአብሔር ፊት ጽና፡፡