“ጉዳዬ አይደለም” ማለትን ተማር

“ጉዳዬ አይደለም” ማለትን ተማር

እንዳይፈረድባችሁ አትፍረዱ ፤ በምትፈርዱበት ፍርድ ይፈረድባችኋልና፤ በምትሰፍሩበትመወ መስፈሪያ ይሰፈርባችኋል፡፡ – ማቴዎስ 7፡1

በየቀኑ የሚገጥሙን ሺ ነገሮች ልክም ወይም ልክም ላይሆኑ ይችላሉ ነገር ግን የግል ምርጫዎች ናቸው ከውጭ ግፊት እና ተጽዕኖ በነጻነት ሰዎች የሚመርጧቸው ናቸው፡፡

ዲያቢሎስ ክፉ መናፍስቶችን በማሰማራት ፈራጅ እና የአበክሮ ምልከታን በሰዎች ልቦና ውስጥ ያሳድራል፡፡ በመናፈሻ ውስጥ ወይም በገብያ መገበያያ ስፍራች ቁጭ ብሎ ሰዎችን በመመልከት ስለ አለባበሳቸው ፣ የጸጉር አቆራረጥ ፣ አሰራር እና ሌሎችም ነገሮች በአዕምሮዬ ውስጥ አሳብ መስጠት ያዝናናኝ እንደነበር አስታውሳለሁ፡፡ ይሁን እንጂ መጽሐፍ ቅዱስ ሰዎች ላይ መፍረድ ትክክል አይደለም ይላል፡፡

ራሳችንን አስተያየት ከመስጠት እና በውስጣችን ልዩ ልዩ ሀሳቦችን ማመላለስ እና ማሰባችን በራሱ ስህተት አይደለም ይህንንም ከማድረግ ራሳችንን ማገድ ይሳናነል ነገር ግን ሌሎች እኛ የምናስበውን ወይም የምንመረጠውን ባለመምረጣው በሰዎች ላይ መፍረድ ፈጽሞ ትክክል አይደልመለም፡፡

በእንደዚህ ዓይነት ሁኔታዎች ጊዜ ጆይስ ይህ ያንቺ ጉዳይ አይደለም ብዬ ለራሴ አስባለሁ፡፡ በውስጣችሁ ክፉ ፈራጅነት እንዲያቆጠቁጥ አትፍቀዱለት፡፡ እግዚአብሔር ሰዎችን ልዩ ልዩ አድርጎ እንደፈጠራችው ሰዎች በተለየ መንገድ ቢያስቡ አትፍረዱባቸው፡፡ ባይሆን ይህ የኔ ጉዳይ አይደለም ማለትን አሰቡበት፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግአዚበሔር ሆይ በሌሎች ላይ መፍረደም ሆነ ትችትን መሰንዘር አልፈልግም፡፡ ከእኔ የተለየ አመለካከት ወይም አስተሳሰብ ያለቸው ሰዎች በገጠሙኝ ግዜ አቤቱ አነት በምታይበት እይታ እኔም እንዳያቸው አግዘኝ፡፡ የኔ እይታ እና አስተያየት ከነሱ ይልቅ ጠቃሚ አለመሆኑን አስታውሰኝ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon