ፀልይ ደግሞም አመስግን

ፀልይ ደግሞም አመስግን

ዳንኤል ደብዳቤው መፈረሙን ባወቀ ጊዜ ወደ ቤቱ ገባ፣. . . በፊት ያደርገው እንደነበረው በቀን ሦስት ጊዜ በጉልበቱ ተንበርክኮ በአምላኩ ፊት አመሰገነ። (ዳንኤል 6:10)

የእግዚአብሔርን ድምፅ ለመስማት እግዚአብሔርን ማመስገን በጣም አስፈላጊ ነው፤ምክንያቱም እንደ ውዳሴ እና አምልኮ ሁሉ እግዚአብሔር ምላሽ የሚሰጥበት ጉዳይ ነው። እግዚአብሔር የሚወደው፣ ልቡንም የሚያሞቅ ነገር ነው። እንደዚያ ደግሞ እግዚአብሔርን ደስ በምናሰኝበት በማንኛውም ጊዜ፣ ከእሱ ጋር ያለን ቅርበት ይጨምራል ይህ ደግሞ ከእርሱ ጋር የተሻለ ግንኙነት እንዲኖረን ያደርጋል።

ባለን ነገር የማናመሰግን ከሆነ ለምን ለማጉረምረም ሌላ ነገር ይሰጠናል? በሌላ በኩል፣ እኛ ለትንሹም ለትልቁም ከልብ ስንደሰትና ስናመሰግነው ሲያይ እግዚአብሔር የበለጠ እኛን ሊባርከን ይፈልጋል። እንደ ፊልጵስዩስ 4፥6 ከሆነ እግዚአብሔርን የምንለምነው ነገር ሁሉ ምስጋናን ያስቀደመና ከምስጋና ጋር አብሮ መሆን አለበት። ስለ ምንም ጉዳይ ይሁን የምንጸልየው፣ ምስጋና ሁል ጊዜ አብሮ መኖር አለበት። ልናዳብረው የሚገባን ጥሩ ልማድ ጸሎታችንን ሁሉ በምስጋና መጀመር ነው። የዚህ ምሳሌ የሚሆነው: – “በሕይወቴ ስላደረግከው ሁሉ አመሰግናለሁ። አንተ ግሩም ነህ እና በእውነት እወድሃለሁ ደግሞም አመሰግንሃለሁ።”

ለሐሳቦችህ እና ለቃሎችህ ትኩረት በመስጠት ምን ያህል አመስጋኝ እንደሆንክ ህይወትህን እንድትመረምረው አበረታታሃለሁ። ራስህን መፈተን ከፈለግህ አንድ የማጉረምረም ቃል ከአፍህ ሳይወጣ ቀኑን ሙሉ ለማሳለፍ ሞክር። በእያንዳንዱ ሁኔታ ውስጥ የምስጋና ዝንባሌን አዳብር። በእርግጥ፣ ሲበዛ አመስጋኝ ሁን-እናም ከእግዚአብሔር ጋር ያለህ ቅርበት ሲጨምር እና ከመቼውም ጊዜ በበለጠ ብዙ በረከቶችን ወደ ህይወትህ ሲያፈስ ተመልከት።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ የማጉረምረምን ሳይሆን የምስጋና ቃላትን ተናገር።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon