ሁላችንም ልጆች ተደርገናል

ሁላችንም ልጆች ተደርገናል

«ዓለም ሳይፈጠር፥ በፊቱ ቅዱሳንና ነውር የሌለን በፍቅር እንሆን ዘንድ በክርስቶስ መረጠን። በበጎ ፈቃዱ እንደ ወደደ፥ በኢየሱስ ክርስቶስ ሥራ ለእርሱ ልጆች ልንሆን አስቀድሞ ወሰነን» (ኤፌ. 1፡ 4– 5)።

ከባለቤቴ ዴቭ (ዳዊት) ጋር ስንገናኝ እኔ የሃያ ሶስት ዓመት ዕድሜ ያለኝና የዘጠኝ ዓመት ዕድሜ ከነበረኝ ልጅ ጋር ነበር። ይህ ልጅ በዝሙትና በክህደት ምክንያት ከተፋታሁት ከመጀመሪያው ባለቤቴ የተገኘ ልጅ ነበር።

ባለቤቴ ዴቭ እንዳገባው ሲጠይቀኝ እኔ የመለስኩለት መልስ «መልካም ታውቃለህ አይደለም እኔ ወንድ ልጅ አለኝ፣ እኔን የምታገባኝ ከሆነ እርሱንም መውሰድ አብረህ መውሰድ አለብህ» የሚል ነበር። ዴቭም አንድ ሚያስደንቅ ነገር ተናገረኝ « ስለልጅሽ የማውቀው ነገር የለኝም፤ እኔ የማውቀው ነገር ቢኖር አንቺን ማፍቀሬ ነው። አንቺን የማፈቅር ከሆነ ደግሞ እኔ ያንቺ የሆነውን ሁሉ መውደድ አለብኝ» አለኝ።

ዴቭ ልጄን እንደልጁ አድርጎ ሲወስደው ሰዎች በጣም ነበር ተደነቁ። እነርሱም ደጋግመው የሚጠይቁት ነገር ቢሆን እንዴት ነው አባት ልትሆነው የወደድከው፤ ይህ ዓይነት ነገር በአካላዊ እይታ የማይቻል ነው፣ ምክንያቱም ዴቭ የእርሱ ዘር በውስጡ ስለሌለ ነበር።

እግዚአብሔርም እንደ ልጆቹ አድርጎ ሲቀበለን ወሳኝ በሆኑ መንገዶች እርሱን እንድንመስል ሊረዳን ፈልጎ ነው። እንደ ልጆች ከመደረጋችን አስቀድሞ በምንም ዓይነት መንገድ እርሱን አንመስልም፤ ነገር ግን ልክ እንደ ማደጎ ልጆች የጉዲፈቻ ወላጆችን ባህርይ መውሰድ ይጀምራሉ። ከእርሱ ጋር ባለን ህብረትና ግንኙነት እያደግን ስንሄድ እኛም የእግዚአብሔርን ባህርያት መውሰድ እንጀምራለን።

በእግዚአብሔር ቤተሰብ ውስጥ ማደጎ ወይም እንደ ልጆች ስንደረግ እኔ በምንም ዓይነት መንገድ የሰማዩን አባቴን አልመስልም ነበር። ነገር ግን ዓመታት እያለፉ ሲሄዱ ግን እየተለወጥኩ ሄድኩና አሁን ሰዎች በእኔ ውስጥ የሰማዩን አባት የሚመስሉ የህይወት ገጽታዎች ውም መልኮች በእኔ ማየት እንደሚችሉ ተስፋ አደርጋለሁ። አሁን በፍቅር፣ በትዕግስት፣ ከሰዎች ጋር ባለኝ ህብረት በጸጋፀ በአመስጋኝነትና በሌሎች ብዙ ነገሮች አደግሁኝ። እግዚአብሔር በህይወትህና አንተ በምትወዳቸው ሰዎች ህይወት ውስጥ ተመሳሳይ ዓይነት ለውጥ ሊያመጣ ይፈልጋል።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ አንተ ዘወትር (ሁልጊዜ) የእግዚእበሔርን መልክ ወደ መምሰል ህይወት በየቀኙ ትሠራለህ

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon