ለመስማት ተቸግረሃልን?

ለመስማት ተቸግረሃልን?

ይህን ስል ስለ ጉድለት አልልም፤ የምኖርበት ኑሮ ይበቃኛል ማለትን ተምሬአለሁና። መዋረድንም አውቃለሁ መብዛትንም አውቃለሁ፤ በእያንዳንዱ ነገር በነገርም ሁሉ መጥገብንና መራብንም መብዛትንና መጉደልን ተምሬአለሁ። (ፊሊጵሲዩስ 4:11–12)

መንፈስ ወደ በረከት ሲመራን ሁል ጊዜ ለመታዘዝ ፍቃደኞች እንሆናለን፣ ይሁን እንጂ ምሪቱ እኛ ወደምንፈልገዉ ካልሆነእሱን“ለመስማት እንቸገራለን”፡፡

ጳዉሎስ ከተለወጠና በመንፈስ ቅዱስ ከተጠመቀ በኋላ፣ ሊገጥሙት ስለሚችሉት ችግሮችና መጽናትእንደሚገባዉከመንፈስ ቅዱስ ሰማ፡፡ (ሐዋ 9:15–16 ተመልከቱ)፡፡ ጳዉሎስ በብዙ አስቸጋሪ ሆኔታዎች ዉስጥ አልፏል፣ ይሁን እንጂ በህይወት ዘመኑም ተባርኳል፡፡ በመለኮታዊ መገለጥና እርዳታ፣ አብዘኛዉን የአዲስ ኪዳን ክፍሎች ሊጽፍ ችሏል፡፡ ራዕይ አይቷል፣ በመልአክት ተጎብኝቷል፣ ሌሎችም ብዙ አስደናቂ ነገሮችንም እንደዚሁ፡፡ነገሮች ሁሉ በበረከት የተሞሉ ባልነበሩበትም ጊዜ እንኳ የመንፈስ ቅዱስን ምሪት መከተል ነበረበት፡፡ ነገሮች የሚስማሙ ወይም የማይስማሙ፣ የሚመቹ ወይም የማይመቹ፣ የሚጠቅሙ ወይም የማይጠቅሙበነበሩበት ጊዜ ሁሉየእግዚአብሔርን ድምጽ ይታዘዝ ነበር፡፡

በዛሬዉ ቃል፣ ጳዉሎስ በረከትን ሲያገኝም በፈተናም ሲገጥመዉ በጽናት ይመላለስ እንደነበር ጽፏል፡፡ በሚቀጥለዉ ክፍል ዉስጥ ደግሞ፣ እነዚህን ሁሉ ኃይልን በሰጠዉ በክርስቶስ እንዳደረጋቸዉ፡፡ በመልካም ጊዜም ሆነ በአስቸጋሪ ሁኔታዎች ዉስጥ ሁሉ ስሜቱን ጠብቆ እንዲቆይ ጥንካሬን አግኝቶ ነበር፡፡

መንፈስ ቅዱስ በአስቸጋሪም ሆነ በመልካም ሁኔታ ዉስጥ ይመራናል፡፡በህይወታችን ለሚሆነዉ ነገር ሁሉ ኃላፊነቱን ለእግዚአብሔር መስጠት አለብን፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ሁኔታዎቻችን ምንም አስቸጋሪ ቢሆኑም እንኳ፣ እግዚአብሔር አይለወጥም፡፡ ለዚህም ሁልጊዜ ምሰጋና እና ክብር ይገባዋል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon