አባትህ ካንተ ጋር መነጋገር ይፈልጋል

አባትህ ካንተ ጋር መነጋገር ይፈልጋል

አባ አባት ብለን የምንጮኽበትን የልጅነት መንፈስ ተቀበላችሁ እንጂ እንደገና ለፍርሃት የባርነትን መንፈስ አልተቀበላችሁምና። (ሮሜ 8:15)

መንፈስ ቅዱስ የልጅነትን መንፈስ የሚሰጠን ነዉ፡፡ ይህን ስንል ከንፈስ ቅዱስ ኃይል የተነሳ የእግዚአብሔር ቤተሰቦች ሆነናል፡፡ ከዚህ በፊት ኃጢያተኞችና ዲያቢሎስን ስናገለግል የነበርን ነን፣ ነገር ግን አሁን እግዚአብሔር ዋጅቶናል፣ በልጁም ደም ገዝቶን፣ የተወደዳችሁ ሴትና ወንድ ልጆቼ ብሎ ጠርቶናል፡፡

ልጆች መሆን አስደናቂ ነገር ነዉ! አንድ ሰዉ ልጅ ሲፈልግ፣ የሚፈልገዉን ሰዉ የራሱ ያደርጋል በፍቅርም፡፡ ይህ ከቤተሰብ መወለድም የተሻለ እድል ነዉ ምክንያቱም እንዳንድ ጊዜ ልጆች ሳይፈለጉ ሊወለዱ ይችላሉና፡፡ አንዳንድጊዜ ልጆች ከወላጆች ቁጭት የተነሳ ሊወለዱም ይችላሉ፡፡ ልጆች በጉዲፈቻ ሲወሰዱ ግን፣ ተፈልገዉ፣ተለይተዉና በአላማ ተመርጠዉ ነዉ፡፡

መታመናችንን በክርስቶስ ኢየሱስ ካደረግን፣ አዲስ ፍጥረት እንሆናለን ይህ ደግሞ የእግዚአብሔር ቤተሰብ እንድንሆን ያደርገናል፡፡ እሱ አባታችን ይሆናል፤በክርስቶስ ኢየሱስ የእግዚአብሔር ወራሾች እንሆናለን፡፡ (ሮሜ 8:16–17 ተመልከቱ)፡፡ አፍቃሪና ፍጹም አባት ይሆነናል፡፡ መልካም አባት ልጆቹን ዝም አይልም፡፡ ብዙ ነገሮችን ለልጆቹ ያደርጋል፣ እግዚአብሔርም እንደዚሁለእኛ ያደርጋል፣ ልክ እንደ አባት፤ ለልጆቹ ፍቅሩን እንደሚገልጽላቸዉ፣ እንደሚመራቸዉ፣ እንደሚያስጠነቅቃቸዉ፣ እንደሚያበረታታቸዉ፡፡ አንተ የእግዚአብሔር ነህ፣ አሳድጎሃል፣ አንተም ልጁ ነህ፤ ዛሬ ሊናገርህ ይፈልጋል፡፡ በወለዱህ ወላጆች የተተወክ እና የተረሳህ ቢመስልህም፣ እግዚአብሔር አባት ሊሆንህ፣ የራሱ ልጅ እንድትሆን እንደወሰደህ ዛሬ ላሳስብህ እወዳለሁ፡፡ (መዝ 27፡10) ተመልከት፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ እግዚአብሔር አንተ ለሱ ልዩ ሰዉ እንደሆንክ ያስባል፡፡ የሱ የራሱ ልጅ እንድትሆንም መርጦሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon