ለማገልግል ድነሃል

« … እንግዲያስ ጊዜ ካገኘን ዘንድ ለሰው ሁሉ ይልቁንም ለሃይማኖት ቤተ ሰዎች መልካም እናድርግ» (ገላ.6፡10)።

ቀንህን ስትጀምር በዛሬው ቀንና በሁሉም ቀናት ሌሎችን ለመርዳት ምን ማድረግ እንደምትችል እግዚአብሔርን ጠይቅ። እኛ በእግዚአብሔር የዳንነው እርሱንና ሌሎችን ለማገልገል እንድንችል ነው። እግዚአብሔር በመጀመሪያው ለአዳምና ለሔዋን ያላቸውን ሀብት ሁሉ በመጠቀም እግዚአብሔርንና ሰዎችን እንዲያገለግሉ ተናገራቸው። ታላቅ ወንድና ሴት የሚባሉት የሚያገለግሉ ናቸው። መሪዎችም ጭምር አገልጋይ መሪ መሆን ይጠበቅባቸዋል።

የኢየሱስ ደቀመዛሙርት ከእነርሱ መካከል ታላቅ ማነው ብለው በጠየቁት ጊዜ እርሱ የመለሰላቸው መልስ ከእነርሱ ታላቅ መሆን የሚሻ የሁሉም አገልጋይ ይሁን (ማቴ.20፡26 ተመልከት)። ከእግዚአብሔር ለመስማት ፍላጎቱን አለህን? አዎችነ ከሆነ፣ ልትረዳቸውና ልትባርካቸው የምትቸለውን እንዲናገርህ እግዚአብሔርን ጠይቀው። እኛ ራሳችንን የሚረዳንን ብቻ ከእግዚአብሔር ለመስማት የምነፈልግ ከሆነ፣ እርሱ ምንም ነገር ላይናገረን ይችላል ምክንያቱም ራሳችንን ብቻ ለመርዳት በምናደርገው የራስ ወዳድነት እርሱ ምንም ፍላጎት የለውም። እኛ በእውነት ለሌሎች የምናስብና ሌሎችን ለማገልገል በምናደርገው ጥረት ውስጥ የእኛ የራሳችን ችግር ያለእኛ ጥረት በእግዚአብሔር መለኮታዊ እጅ መፍትሔ አግኝቶ እናገኛለን።

በእግዚአብሔር መንግስት ውስጥ « የአገልጋይነት» ሥፍራ ከፍተኛውን ሥፍራ የያዘ ነው። ክርስቶስ እንዲያገለግል እንጂ እንያገለግሉት አልመጣም (ማር.10፡45 ተመልከት)። አንድ ሰው ፈቃደኛ ከሆነ ማገልገል ይችላል። አሁን ሰዎች የሚፈልጉትን፣ የሚያስፈልጋቸውንና የባከነ ህወታቸውን የሚሉትን ስማ። አንተ ሌሎችን ስታገለግል ከክርስቶስ ጋር ያለህ መቀራረብ የበለጠ የሚጨምር ይሆናል ምክንያቱም እርሱ አገልጋይ ስለሆነ ነው።


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡ ዛሬ ሌሎች ሰዎችን ለመርዳት ምን ማድረግ እንዳለብህ ጸልይና እግዚአብሔርን ጠይቅ። ለእረፍት፣ ለትንሹ ድምጽ በሥራ የተጠመደ ታዛዝ ለመሆን ስማው።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon