ቀለል አድርገህ እየው

ቀለል አድርገህ እየው

«ነገር ግን እባብ በተንኮሉ ሔዋንን እንዳሳታት፥ አሳባችሁ ተበላሽቶ ለክርስቶስ ከሚሆን ቅንነትና ንጽሕና ምናልባት እንዳይለወጥ ብዬ እፈራለሁ» (2ኛቆሮ.11፡3)።

እግዚአብሔር በትክክል የሚፈልገው ከእርሱ ጋር ያለን ህብረትና ግንኙነት ቀለል ያለ እንዲሆን ነው፣ ነገር ግን ዲያቢሎስ ስለ ጸሎት ያለውን ሃሳባችንን ይጠመዝዘዋል፣ ምክንያቱም ይህ ዓይነት የጸሎት ህብረት ያለውን ኃይል ስለሚያውቀው ብቻ ሳይሆን በተጨማሪም እርሱ እኛ ያለንን ህብረት ስለሚያውቀው ነው።

አሁን ራስህን መጠየቅ ያለብህ « እግዚአብሔር ሲፈጥረን ከእርሱ ጋር ህብረትና ግንኙነት እንድናደርግ እንደሚፈልግና ከዚያስ ለምን ነገሮች ውስብስብ እንደሆኑ ነው»። እግዚአብሔር ምንም ነገር ማወሳሰብ አይፈልግም። እርሱ ስንጸልይና ከእርሱ ጋር ጊዜ ስናሳልፍ ቀላል እንዲሆንልንና ደስተኛ እንድንሆን ነው ያደረገው። ሰይጣን እኛ ጸሎት ረዘም ያለ ጊዜ እንደሚፈልግና የተወሰነ ቀመር (ሥርዓት) እንደሚፈልግ እንድናምን ይፈልጋል። ሰይጣን ጸሎታችንን በመመሪያና በሥርዓት ይከብብ ወይም ይሸፍንና ስንጸልይ እግዚአብሔር እንድንደሰት የሚፈልገውን ነጻነትና አዲስ ልምምድ ይሰርቅብናል። እርሱ የሚጥረው እምነት እንዳይኖረን ሊያቅበንና እንዲሁም በምንም ዓይነት መንገድ ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ የበቃን እንዳይደለን፤ የእግዚአብሔርንም ድምጽ ለመስማት እንደማንችል በትክክል ሊያሳምነን ይጥራል።

ዲያቢሎስ ሁልጊዜ የሚጥረው ስንጸልይ እኛን እየከሰሰ ትክክለኛና በቂ ጸሎት እንዳልጸለይን ወይም በትክክለኛ መንገድ እንዳልጸለይን፣ እንዲሁም ጸሎታችን ምንም ዓይነት ነገር መፍጠር እንደማይችል ይነግረናል። እርሱ በተጨማሪ የሚፈልገው ስንጸልይ ህይወታችንን ሊረብሽ ይፈልጋል። ከዚህ የተነሳ ሰዎች ብዙውን ጊዜ ጸሎት ከባድ ነገር እንደሆነ እንዲሰማቸውና እንደምንም ጥረው የሚያደርጉት ጸሎት እንደማይሳካላቸው እንዲያስቡ ያደርጋል።

በአጠቃላይ ብዙ ሰዎች በጸሎት ህይወታቸው ተስፋ የቆረጡና ምንም ደስተኞች እንዳልሆኑ ይመስላል፤ ነገር ግን ይህ መለወጥ ይቻላል። እኛ ቀለል ያለ ጸሎት፣ ከልባችን ተሰምቶን፣ የእምነት ጸሎት መጸለይና እግዚአብሔር እንደሚሰማንና እንደሚመልስልን እርግጠናኛ መሆን አለብ


ላንተ የሆነው የዛሬው የእግዚአብሔር ቃል፡ ወንድሜ(እህቴ) ላንተ መልካም ዜና አለኝ ተረጋጋ ቀለል አድርገህ ያዝ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon