ቀድመህ ሂድና ጠይቅ

ቀድመህ ሂድና ጠይቅ

«በእርሱ ዘንድ ያለን ድፍረት ይህ ነው፤ እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ይሰማናል» (1ኛ ዮሐ.5።14)።

ወደ እግዚአብሔር ለመጸለይ ስንቀርብ በድፈረት በመሞላት እንዲሆን ላበረታታህ እወዳለሁ። እግዚአብሔር ደስ እያለን እንድንጸልይና ስህተትን አደርጋለሆ ብልን እንድንፈራ አይፈልግም። እንደ ፈቃዱ አንዳች ብንለምን ጸሎታችንን ሊሰማና ሊመልሰልን ቃል ገብቶልናል። ነገር ግን አንዳች እንደ ፈቃዱ ያለሆነውን ጸሎት ግን ምን ያደርጋል? ባለን አቅም ሁሉ እንደ ፈቃዱ የሆነውን ጸሎት እንድንጸለይ ያስፈልገናል። ነገር ግን ጠላት ከመጠን በላይ በሆነ ፍርሃት በልባችን ያለውን ጸሎት ወደ እግዚአብሔርን ለመጸለይ በማፈር ህይወታችንን ያጠምድ ዘንድ መፍቀድ የለብንም።

ከእግዚአብሔር ፈቃድ ውጪ የሆነውን ጸሎት ስንጸልይ በጣም መልካም ያለሆነ ነገር ይሆናል የምንጠይቀውንም ነገር አናገኝም፤ ይህ ደግሞ እግዚአብሔር ለእኛ ያለው ፍጹም በጎነት ነው። እግዚአብሔር ልባችንን ያውቃል፤ እንዲሁም እርሱ ከእርሱ ፈቃድ ውጪ የሆነውን ብንለምነውና ስህተትን ብንፈጽም ምንም የሚቆጣን አይሆንም። ወደ እርሱ ቀርበን በምንጸልየው ጸሎት ስህተትን ልፈጽም እችላለሁ የሚል ፍርሃትና በምጸልየው ብዙ ጸሎቶች እርሱን ደስ ላሰኘው አልችልም በሚል መቅረብ አያስፈልገንም። እኔ ለምሻውና ለምፈልገው ነገር እግዚአብሔርን ለምጠይቀው ጸሎት መንገዴ በተቻለ መጠን ሁልጊዜ በእግዚአብሔር ቃል ላይ የተመሠረተ መሆን አለበት። ከዚያም «እግዚአብሔር ሆይ ማንኛውንም እኔ የምጠይቅህ ነገር ለእኔ ትክክል ላይሆን ይችላል፣ ነገር ግን ለእኔ አሳልፈህ እንደማትሰጣቸው አንተን አምንሃለሁ» ወደ እርሱ በእምነት፣ በድፍረት ሂድ፤ የእርሱን መልስ በእምነት ተጠባበቅ።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ወደ ፊት ሂድና ጠይቅ

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon