እግዚአብሔርን መጠበቅ

እግዚአብሔርን መጠበቅ

«በእግዚአብሔር ፊት ጸጥ በል፤ በትዕግስትም ተጠባበቀው» (መዝ.37፡7)

እኔ ከእግዚአብሔር ሁልጊዜ መስማት እፈልጋለሁ እንዲሁም ስለሁሉም ነገር ከእርሱ መስማት እሻለሁ። እግዚአብሔርን ለመስማት ከማንኛውም ነገር ይልቅ ከውስጥ ረሃብ (ቅናት) በሚወጣ ጥበብ እርሱን ለመጠበቅ የእግዚአብሔርን ፈቃድ ለመፈለግ ፈቃደኛ መሆን ግድ ይላል። የምንወስዳቸው እርምጃዎች በሥጋዊ ፍላጎቶችና ስሜታዊነት ተመስርቶ የተወሰነ እንዳይሆን ከእግዚአብሔር መስማት በግልጥ መሆን አለበት። በሁሉም አቅጣጫ እርምጃ ከመውሰዳችን በፊት ከእግዚአብሔር የምናገኘው ምሪት ላይ ሙሉ ድፍረት እንዲኖረን በእግዚአብሔር ፊት ብንቆይ እንባረካለን። በመቀጠል ምንም እንኳን ለመፈጸም ለእኛ አስቸጋሪ ቢሆንም እግዚአብሔር እንድናደርግ የሚፈልገውን ነገር ማድረግ ይጠበቅብናል።

ከብዙ ዓመታት በፊት ታዋቂነት ያላቸው ፊልሞችን ማሰባሰብ ጀመሬአለሁ፣ ምክንያቱም በቴሌቪዥን ሲታዩ ምንም ነገር ጨዋነት ሥነምግባር አይታይባቸውም ነበርና። አንድ ቀን ግን አንድ መጽሔት መልካም፣ ንጽህና ያላቸው ፊልሞች ዝርዝር ወደ ቤቴ ላከልኝ። እግዚአብሔር ብዙ ፊልሞችን እንዳገኝ በላፕቶፔ ላይ የጨመረልኝ ዕድል ይመስላል። እኔም በጣም በመደነቅ ወደ አስራ አምስት ፊልሞችን ያህል ወስኜ እንዲልኩልኝ አዘዝኩ። ነገር ግን እኔም ከማዘዣው ጎን ለጎን ለጥቂት ቀናት አዘዝኩና ከዚያም ደግሜ ስመለከታቸው ስሜቴና አድናቆቴ እየቀነሰ መጣና እኔም ሁለት ፊልሞችን ብቻ ወደ ማዘዝ ወሰንኩ። ይህ ቀላል ምሳሌ ነው፤ ነገር ግን ይህ መርህ በሁሉም የህይወታችን ክፍል ላይ የሚተገበር ነው።

ሁልጊዜ በስሜት መነሳሳት ብቻ ላይ እርምጃ የምንወስድ ከሆነ ብዙውን ጊዜ ስህተትን እንፈጽማለን። እኔም እንዲህ እላለሁ «ስሜትህ ጋብ ሲል ከዚያም ውሳኔህን ወስን»። ስለነገሮች ጥሩ ስሜት እንዲሰማን የማታ ጥሩ እንቅልፍ ምንኛ የሚያስደንቅ ልዩነት የሚፈጥር ነው።

እኔ ዛሬ የማደፋፍርህ በእግዚአብሔር ፊት መቆየትን መማር እንዳለብህ ነው። ስሜት ከፍ ይላል እንዲሁም ይወርዳል፣ እናም ስሜታዊ ኃይል ይመጣና ከፍ ይላል (ይጦዛል)። የተወሰነው ነው እግዚአብሔር ወዳየልን ፍጻሜ የሚመራን። እኛ ከስሜታዊነት ይልቅ የእርሱ ቃልና ጥበብ እንዲመራን ስንፈቅድለት እግዚአብሔር ሁልጊዜ ወደ ተሻለ መልካም ሥፍራ የሚመራን ይሆናል።


ላንተ የሆነው የዛሬው የእግዚአብሔር ቃል፡ ስሜትህ ወደ ጎን ብለህ ትክክለኛ ውሳኔ ወስን።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon