እግዚአብሔር ሁልጊዜ እንድንቀደስ ይፈልጋል

እግዚአብሔርከኅጥኣንይርቃል፤ የጻድቃንንጸሎትግንይሰማል።  (ምሳሌ 15:29)

በዛሬዉ ቃል እኛ በመንገዳችን ሁሉ ከእግዚአብሔር ጋር ለመሆን ታማኞች ከሆንን፣ እሱ ጸሎታችንን እንደሚሰማን ቃል ይገባልናል፡፡ “ሁል ጊዜ መቀደስ” ማለት ምን ማለት ነዉ? ይህን በቀላሉ ስንገልጸዉ፣ ሁል ጊዜ ለመቀደስ አለመመቻመች ነዉ ብዬ አስባለሁ፡፡

የሚያመቻምች ሰዉ፣ ትክክለኛ ነገር እንኳ ባይሆንም ማንኛዉም ሰዉ የሚያደርገዉን ለማድረግ ወደኋላ የማይል ሰዉ ነዉ፡፡የሚያመቻምች ሰዉ ትክክለኛ ያልሆነዉን ነገር ያዉቃል፣ ነገር ግን ባደርገዉ አንድ ነገር አገኛለሁ ብሎ ስለሚያስብ ከማድረግ ወደኋላ አይልም፡፡ የምናመቻምቸዉ፣ የምናደርገዉ ነገር ትክክል አለመሆኑን በልባችን እያወቅነዉ መንፈስ ቅዱስም እየወቀሰን ነዉ፡፡ ይህንን ስንል፣ “እግዚአብሔር ማድረግ ያለብኝን ሲነግረኝ፣ አኔ ደግሞ ደስያለኝን ነገር ማድረግ ማለት ነዉ፡፡” በዚህ ምክንያት ለማግኘት የምንፈልገዉን ካላገኘን፣ ስህተቱ ያራሳችን ነዉ፡፡ ካላመቻመችንና ሁል ጊዜ በቅድስና ለመመላለስ ከቆረጥን፣ እግዚአብሔር ልባችንን ያያል፣ ጸሎታችንንም ሰምቶ ይመልሳል፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ ፡ ካላመቻመችክ፣ እግዚአብሔር ባንተ ደስ ይለዋል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon