ለአምላክህም ለእግዚአብሔር ቃል ታዘዝ ዛሬም የማዘዝህን ትዕዛዙንና ሥርዓቱን አድርግ፡፡ ዘዳ 27÷10
እግዚአብሔር አንዳንድ ጊዜ እንደምታውቀው በሌሎች ሰዎች በኩል ይናገረናል የሆነ ጊዜ እግዚአብሔር በሕይወቴ ጉዳይ በዴቭ (በባለቤቴ) በኩል ተናገረኝ፡፡ መልዕክቱን ሲነግረኝ ተናደድኩ፡፡ ዴቭ በቀላሉ፡- ‹‹አንቺ የወደድሽውን መሆንና ማድረግ ትችያለሽ እኔ ግን የምነግርሽ እግዚአብሔር እንዳሳየኝ የማምነውን ነው፡፡›› አለኝ፡፡ የነገረኝ እውነት መሆኑን ሊያሳምነኝ አልሞከረም እርሱ በቀላሉ እግዚአብሔር ለእርሱ እንደተናገረ የሚያምነውን አቀረበ፡፡ ከሶስት ቀናት በኋላ ዴቭ የተናገረኝ ትክክል እንደነበር እግዚአብሔር አሳመነኝ፡፡ ዴቭ የተናገረኝ ትክክል መሆኑን ለመቀበል በማፈሬ ብዙ አለቀስኩ፡፡
እግዚአብሔር በዴቭ በኩል በእውቀት ቃል ሲናገረን በሕይወቴ ውስጥ የሚያስጨንቀኝን ጉዳይ ለመረዳት ችያለው፡፡ እኔ የፈለኩት እግዚአብሔርን እንጂ የትኛውንም ዓይነት ለትግሬ የሚሆን መልስ ወይም መፍትሔን አልነበረም፡፡ ዴቭ የእኔ መልስ የሚሆን ሰጥቶኛል፡፡ ነገር እኔ ልሰማው አልፈለኩም፡፡ ምክንያቱም ዝም ብሎ የሚያወራ በኃጥያት የሚከሰኝ የሚወነጅለኝ መሰለኝ፡፡ እኔ ልሰማው ያልፈለኩበት እውነት ለምን እግዚአብሔር ሚሥጥሩን ለጄቭ ሰጠ፡፡ ምክንያቱም እኔ ከእርሱ እንደማልሰማ ያውቃልና ነው፡፡
ይህ ልምምድ በሕይወቴ ምን ዓይነት ተጽዕኖ እንዳመጣ ለማጋነን አልፈልግም እግዚአብሔር ከእኔ ጉዳይ ጋር በቀጥታ ገብቶ ነበርና እርግጠኛ ሆኜ የምናገረው ከዚህ ጉዳይ የተማርኩት ከዚህ በፊት የተማርኩት ዓይነት አልነበረም በዴቭ በኩል የተነገረኝ፡፡
ልብህን ከፍተህ እግዚአብሔር ታማኝ በሆኑና አንተን በሚወዱ እንዲሁም ድምፁን በትክክል ሰምተው እርሱ ለአንተ ለማለት የፈለገውን የሚነግሩህን ትሰማ ዘንድ አበረታታለሁ፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- እርሱ ደስ ደስ በሚያሰኝ በማንም፣ የትም፣ እንዴትም ሆኖ በየቀኑ እንዲናገርህ እግዚአብሔርን ጠይቀው፡፡