አእምሮ፣ ፈቃድና ስሜት

አእምሮ፣ ፈቃድና ስሜት

እንድያስተምረው የጌታን ልብ ማን አውቆት ነው; እኛ ግን የክርስቶስ ልብ አለን፡፡ 1 ቆሮ 2÷16

ኢየሱስን ወደ ልባችን እንዲመጣ ስንጋብዘው መንፈስ ቅዱስ በእኛ ውስጥ መኖሪያ ያደርጋል፡፡ ከዚያ የልባችን ዙፋን ውስጥ የሕይወታችን ማዕከል መንፈስ ቅዱስ ነፍሳችንን ማጥራት ይጀመራል፡፡ (አእምሮአችነን፣ ፈቃዳችንንና ስሜቶቻችንን)፡፡

አእምሮአችን ምን እንደምናስብ ይነግረናል፡፡ እግዚአብሔር የሚያስባውን አይደለም፡፡ መንፈስ ቅዱስ በሕይወታችን የምሰራው ያንን ለመለወጥ ነው፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ተስማምተን ለማሰብ እንድንችል መማር አለብን፡፡ እንዴት እግዚአብሔር ሃሣቡን የምፈፅምበት ዕቃ (መሣሪያ) ለማሆን እንድንችል እናስባለን፡፡ አሮጌ ሃሣቦች ከእኛ መጽዳት (መታደስ) አለባቸው፡፡ አዳዲስ ሃሣቦች የእግዚአብሔር ሃሣቦች የእኛ የሃሣብ ክፍሎች መሆን አለባቸው፡፡

የእኛ ስሜት ምንና እንዴት እንደተሰማን ይነግሩናል፡፡ ነገር ግን ለእግዚአብሔር ስለ ሁኔታው ስለ ሰዎችና እኛ ስለ ወሰነው ምን እንደተሰማው አይነግሩንም፡፡ በመዝ 7÷9 መሠረት እግዚአብሔር ስሜታችንን ይፈትናል ደግሞም ይመረምራ፡፡ እርሱ ከእኛ ጋር የምሰራው እኛ በሰውኛ ስሜት እስካልተነዳን ብቻና በመንፈሱ ስንሆን ነው፡፡

የእኛ ፍቃድ እኛ የምንፈልገውን ይነግረናል የእግዚአብሔርን ፈቃድ አይደለም፡፡ ፈቃድ ስሜትን እንዲሁም ሃሳብን ይቆጣጠራል፡፡ ትክክለኛውን ነገር ልንሰራበት እንጠቀምበታለን፡፡ ምንም እንኳ ለማድረግ ፍላጎት በሌለን ጊዜ እንኳ፡፡ ነፃ ፈቃድ አለን እግዚአብሔርም ደግሞ ምንም ነገር እንድናደርግ አያስገድደንም፡፡ እራሱ ለእኛ መልካም መሆኑን ወደሚያውቅ ነገር በመንፈሱ ይመራናል፡፡ ነገር ግን የመጨረሻው ውሳኔ ለማድረግ የእኛ ፈንታ ነው፡፡ እግዚአብሔር ሁልጊዜ በመደበኛነት ከእኛ ጋር በስምምነት ላይ የተመሠረተ የእርሱ ፈቃድ እንዲሆን ይፈልጋል፡፡ የእኛ ፈቃድን አይደለም፡፡

እነዚህ ሦስቱ የሕይወታችን ክፍሎች፡- አእምሮ፣ ፈቃድና ስሜት ከኢየሱስ ክርስቶስ አመራር ሥራና ከመንፈስ ቅዱስ ሥር እየገቡ ሲመጡ እንደ አማኝ በመንፈሳዊ ብስለታችን እያደግን እንመጣለን፡፡


የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- ስሜቶችህን አንተው በመቆጣጠር መግዛት ትችላለህ፡፡ እነርሱ አንተን በመቆጣጠር ከምገዛህ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon