እግዚአብሔር በአንተ ይኖራል

እግዚአብሔር በአንተ ይኖራል

‹‹… በእኔ ኑሩ እኔም በእናንተ። ቅርንጫፍ በወይኑ ግንድ ባይኖር ከራሱ ፍሬ ሊያፈራ እንዳይቻለው፥ እንዲሁ እናንተ ደግሞ በእኔ ባትኖሩ አትችሉም›› (ዮሐ.15፡ 4)።

እግዚአብሔር በእኛ ውስጥ መኖር ለምን ፈለገ በውስጣችንስ እንዴት መኖር ይችላል ከሁሉም በላይ እርሱ ቅዱስ ነው፣ እኛ ደግሞ ደካች ነን፣ የሰው ሥጋ ከነድካሙ፣ ስህተቱና ውድቀቱ ጋር አለ፡፡

መልሱ ቀላል ነው፡ እርሱ ስለሚወደንና በእኛ ውስጥ መኖሪያውን ሊያደርግ ስለወደደ እኛን መኖሪያው አደረገ፡፡ እርሱ እግዚአብሔር ስለሆነ ይህንን አደረገ፤ እርሱ የፈለገውን የማድረግ ኃይል አለው፣ እንዲሁም እርሱ ወድዶና መርጦ መኖሪያውን በልባችን ውስጥ ሊያደርግ ፈለገ፡፡ ይህ ምርጫ በእግዚአብሔር ጸጋ፣ ኃይልና ምህረት ላይ የተመሠረተ እንጂ እኛ ስላደረግነው ወይም ልናደርግ ስለምንችለው መልካም ሥራ ላይ የተመሠረተ አይደለም፡፡ እኛም በክርስቶስ ኢየሱስ በማመን (እግዚአብሔር በመጽሐፍ ቅዱስ ውስጥ እንዳስተማረን) የእርሱ መኖሪያ ሆንን፡፡

የዛሬው የመጽሐፍ ቅዱስ ክፍላችን የሚያተኩረው እውነት እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር የጠበቀ ህብረት ልምምድ እንዲኖረን በላከው በአንዱ በኢየሱስ ክርስቶስ እንድናምን ነው፡፡ በእርሱ ማመን የእርሱን ድምጽ እንደንሰማ ያስችለናል፣ በልባችንም ቃሉን እንድንሰማና የእርሱን ህልውና እንዲሰማን ነው፡፡

በተጨማሪም ኢየሱስ የእግዚአብሔር ለሰው ልጆች ሁሉ ከሰማይ የተላከ ስጦታ እንደሆነ እንድናም የአየሱስ ለኃጢአታችን መስዋዕት መሆን ወደ እግዚአብሔር ህልውና እንድንገባ የሚያስችለን በቂ እንደሆነ በቀላሉ እንድናም ነው፡፡ ኢየሱስ ክርስቶስን የግል አዳኛችን አድርገን ስንቀበል እኛ የእግዚአብሔር መኖሪ እንሆናለን፡፡ ከዚህ አቋም የተነሳ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል በህይወታችን አስደናቂ ሥራ መስራት ይችላል፡፡


ላንተ የሆነው የዛሬው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔር በልብህ እንደሚኖር እንዲሰማው እርግጠኛ ሁን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon