ከሰማይ ካልተሰጠው ሰው አንዳች ሊቀበል አይችልም፡፡ ዮሐ. 3÷27
ሰዎች እርስ በርሳቸው በመንፈሳዊ ሥጦታዎች፣ በተፈጥሮ ችሎታቸውና እግዚአብሔር በእነርሱ ሕይወት ላይ ባደረገው ጥሪ ረገድ ሲወዳደሩና ሲያወዳድሩ ሳይ የሆነ ነገር ይሰማኝና በጣም አዝናለሁ፡፡ ውድድርና ማወዳደር እግዚአብሔር በሕይወታችን ለማድረግ ያቀደውን ዕቅድ እንዳይሆን በማድረግ ያለንና ሊኖረን የሚገባንን ደስታ እንድናጣ ያደርገናል፡፡
የዛሬው ጥቅስ የሚያስተምረን ባለን የፀጋ ሥጦታ ወይም ሥጦታዎች እንርካ ነው፡፡ ሥጦታችን ከእግዚአብሔር የተሰጡን ናቸው፡፡ እኛም እርሱ በሰጠን ስጦታ ደስተኞች ልንሆን ይገባል፡፡ ምክንያቱም እግዚአብሔር ሳይፈቅድ ምንም ዓይነት የፀጋ ሥጦታ ማግኘት ስለማንችል ነው፡፡ መንፈስ ቅዱስን መታመን አለብን፡፡ የእርሱን ፈቃድ በእያንዳንዱ የሕይወታችን ክፍል እንዲያደርግ በመታመን እግዚአብሔር ልኮታልና፡፡
እግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስን በእኛ ውስጥ እንዲኖር የላከውን እውነታ እንድታሰላስል አበረታታሃለሁ፡፡ በመሠረቱ እርሱ በማንኛው በእውነት ጌታን እንደ ግል አዳኙና ጌታ አድርገው በተቀበለው ሰው ውስጥ ይኖራል፡፡ መንፈስ ቅዱስ የተላከው በመጨረስ ቀን ኢየሱስ ተመልሶ የራሱ የሆኑትን እስኪወስደን ድረስ እንዲጠብቀን ነው፡፡ እርሱ ሊናገረን ስለሚሞክር ለእኛ ኢየሱስ ክርስቶስ ወደ ሞተበት ሙላት ይመራናል፡፡ በመጠራታችን፣ በሆነውና ባለን ነገር ስንነጫነጭና ሳንረካ ስንቀር ከመንፈስ ቅዱስ ሥራና ጥበብ ጋር እንጣላለን፡፡ እራሳችንን ለእርሱ ልንሰጥ ይገባናል፡፡ በእርሱ እርዳታም በሕይወታችን ለእግዚአብሔር ክብር በደስታና በሙላት ሊኖርበት ይገባል፡፡
የእግዚአብሔር ቃል ዛሬ ለአንተ፡- መርካት ለእግዚአብሔር ምሥጋናው ነው፡፡ እርሱን እንደምንታመንና ላደረገልን ሁሉ የምናመሰግንበት መልዕክት ለእርሱ አለው፡፡