እግዚአብሔር ይረዳል (ያውቃል)

እግዚአብሔር ይረዳል (ያውቃል)

‹‹…ጌታችን ታላቅ ነው፥ ኃይሉም ታላቅ ነው፥ ለጥበቡም ቍጥር የለውም›› (መዝ.147፡5)።

እኔ ብዙ አንደበተ ርቱዕ ነኝ ብዬ አላስብም እናም የአንተም የግንኙነት መንገድ በጣም የተወሳሰበ ዘመናዊ መሆን እንዳለበት ማሰብ የለብህም፡፡ ከእግዚአብሔር ጋር ስነጋገር ድምጼን እንዴት ማውጣት ተጨንቄ አላውቅም፤ በልቤ ውስጥ ያለውን በቀላሉ ለጌታ እናገረዋለሁ እናም ግልጽ፣ ቀላልና በቀጥታ በሆነ መንገድ እናገረዋለሁ፡፡ይህ ደግሞ ከባለቤቴ ጋር የምነጋርበት መንገድ ዓይነት ነው፤ እንዲሁም ይህ ከልጆቼ ጋር የምነጋገርበት መንገድ ዓይነት ነው፤ ይህ አብሬአቸው ከምሠራቸው ሰዎች ጋር የምነጋገርበት ዓይነት መንገድ ነውና ስለዚህ ይህ ዓይነት መንገድ እኔ ለእግዚአብሔር የምናገርበት መንገድ እንደሆነ ሁሉ እርሱም ለእኔ የሚናገርበት መንገድ ነው፡፡ እኔ በምንም ነገር ላስደንቀው ሞክሬ አላውቅም፤ እኔ በልቤ ውስጥ ያለውን ለእርሱ ማካፈል ነው የምሞክረው እናም በቀላሉ እራሴን ለመሆን የምችለውን ያህል አደርጋለሁ፡፡

እግዚአብሔር እኛ ራሳችንን እንድንሆን ነው የፈጠረን፣ እናም ወደ እርሱ ስንቀርብ ያለምንም ራሳችንን ማታለል መሆን አለበትና እርሱ እንዲሰማን የተወሰነ ጨዋ መንገድ አለ ብለን ሳናስብ መሆን አለበት፡፡ እውነተኛ እስከሆንን ድረስ እርሱ ይሰማናል፡፡ በልባችን ያለው ነገር ምንም እንኳን በተከሸኑ ቃላት የተቀመሙ ባይሆኑም እርሱ ግን አሁንም ይሰማናል እንዲሁም ያለንበትንም ይረዳል፡፡ ወደ እርሱ የሚያቀና ልብ በእርሱ ዓይን ፊት እጅግ የከበረ ነውና ሊነገሩ የማይችሉትን ቃላትንም እንኳን ቢሆን እርሱ ይሰማል፡፡ አንዳንድ ጊዜ ለመጸለይ ስናስብ እጅግ ራሳችንን እጅግ እንጎዳለንና ከዚያም ለመቃተትና ለመጨነቅ እንዳረጋለን፤ እንዲሁም ያም እንኳን ቢሆን እግዚአብሔር ይረዳናል፡፡ ዛሬ እግዚአብሔር እንደሚረዳህ በማወቅ ልትጽናና ትችላለህና እርሱ ሁሉንም ነገር አንተ የምትለውን ይሰማሃል፡፡


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔር ትክክለኛውን ነገር ይወዳል፣ እንደምትጸልየው ሆነህ ተገኝ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon