ጥበብ እየጠራቻችሁ ነው

ጥበብ እየጠራቻችሁ ነው

በመንገድ አጠገብ ባሉ ኰረብቶች፣ መንገዶቹ በሚገናኙበትም ላይ ትቆማለች፤ ወደ ከተማዪቱ በሚያስገቡት በሮች አጠገብ፣ በመግቢያዎቹ ላይ፣ ድምጿን ከፍ አድርጋ እንዲህ ስትል ትጮኻለች፤ – ምሳሌ 8፡2-3

በሕይወት ጉዞኣችን በርከት ያሉ ውሳኔዎችን ማሰለፋችን ግልጽ ነው እነዚህ ውሳኔዎች ግን ከስሜት ራቅ ብለን ወይም እንደ ፍላጎታችንና እንደምናስበው የሆኑ ከሆነ ግን ችግር ውስጥ ይከቱናል፡፡ ደህና ውሳኔ እንድንወሰድ እግዚአብሔር ይፈልጋል፡፡ በጥበብ የተሞላ ውሳኔ መውሰደ ማለት ከውሳኔው ማግስት የሚያስደስተንን ነገር አስቀድሞ መምረጥ ማለት ነው፡፡

ምሳሌ እንዲህ ይላል ጥበብ ትጣራለች፡፡ በእግዚብሔር ጥበብ ልንጓዝ ይገባል እና በእርሱ ጥበብ የዛሬው ውሳኔ ነጋችንን እንደሚወስን ይነግረናል፡፡ በርከት ያሉ ሰዎች ጥበብ የጎደላቸው ውሳኔዎችን ከማሳላፋቸው የተነሳ በሕይወት ደስታን ማግኘት አልቻሉም፡፡

በራስ ወዳድነት አንዳች አታድርግ ፣ አትቆምር ደህና ነገር አገኛለሁ ብለህ፡፡ የወደ ፊት ህይወት ላይ ትገነባለች እንጂ ጥበብ አትቆምርም፡፡ ጥበብ በፈጣን እርካታ ላይ አታርፍም። ነገር ግን ለተሸለ ነገ እግዚአብሔርን ትከተላለች፡፡

አንተስ ?፣ ከጥበብ ጋር እየተራመድክ ነው ዛሬ ? ካለሆነ ፤ መልካም ዜና ጥበብ እየጠራችህ ነው፡፡ እግዚአብሔር በጥበቡ ሊባርክህ ፈቃደኛ እና ዝግጁ ነው፡፡ የወደፊቱ ሕይወትህ በመልካም የተገነባ እንዲሆን ወስንና እንዲረዳህ እግዚአብሔርን ጠይቀው፡፡


ጸሎት ማስጀመሪያ

እግዚአብሔር ሆይ ከጥበብ መጉደል የተነሳ በቋሚነት ተግዳሮቶችን ከማራገፍ ይልቅ በሕይወት ደስ መሰኘት እፈልጋለሁ፡፡ ጥበብን ስለምትሰጠኝ አመሰግንሃለሁ፡፡ ሰለመጻኢ ሕይወቴ በጥበብ የተሞሉ ውሳኔዎችን መርጫለሁ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon