ፍርሃትን ተቃወም፣ እምነትን ተሞላ

ፍርሃትን ተቃወም፣ እምነትን ተሞላ

«ለእምነትም ደስ ማሰኘት አይቻልም፤ ወደ እግዚአብሔር የሚደርስ እግዚአብሔር እንዳለ ለሚፈልጉትም ዋጋ እንዲሰጥ ያምን ዘንድ ያስፈልገዋልና» (ዕብ.11፡6) ።

ሰይጣን በዘመናት መካከል በሰዎች ል ሊያደርገው የሚሞክረው ህይወታችንን በፍርሃት መሙላት ነው። እግዚአብሔርን በእምነት መስማት ከጀመርንበት ጊዜ አንስቶ ፍርሃትን በሙሉ ኃይላችን መቃወም ይገባናል። መጽሐፍ ቅዱስ እንደሚናገረው የእግዚአብሔር ቃል ከእምነት ወደ እምነት የሚመራ ጽድቅ ይገልጣል ይላል። እኛ በክርስቶስ ያለንን ስፍራ ካወቅንና ምን ያህል እንደሚወድደን ካወቅን ሁሉንም ነገርና ማንኛውንም ነገር ይዘን በእምነት አመለካከት መቅረብ እንችላለን። እግዚአአብሔር በተደጋጋሚ እንደተናገረው እኛ መፍራት የለብንም ምክንያቱም እርሱ ከእኛ ጋር ስለሆነ ነው።

ከእምነት የሆነው ጸሎት እኛንና ሌሎችን በአስደናቂ መንገድ የሚረዳን ነው። ስለዚህ እኔ እምነትህ በጥንካሬ እንድትጠበቅ አበረታታሃለሁ፡፡ የእግዚአብሔርን ፈቃድ የምንቀበለው በእምነት ጸሎት እንቀበላለን፤ ነገር ግን እንዲሁ የሰይጣን ፈቃድ በፍርሃት ውስጥ ልንቀበል እንችላለን። ኢዮብ እንደተናገረው የፈራሁት ነገር መጥቶብኛል ይላል (ኢዮ.3።25) ስለዚህ ከእምነት ወደ እምነት በእርሱ ለመኖር እርግጠኛ ሁን፡፡ እግዚአብሔር መልካም ስለሆነ ከእርሱ ጠብቀህ የምትቀበለው የተሻለ ነገር ሁሉ በእምነት በመቅረብ ነው፡፡

ጸሎት እጅግ አስፈላጊ ከሆኑ ነገሮች መካከል ዋናው ሲሆን በሙሉ ልብ በእምነት መቅረብ ይገባናል፡፡ ይህ ደግሞ የሰማይን መስኮት በመክፈት የእግዚአብሔርን ኃይል በህይወታችንና ባለንበት ሁኔታዎች ላይ እንዲለቀቅ ያደርጋል፡፡ ፍርሃት እምነትህን እንዳያጠቃውና እግዚአብሔር ለአንተ እንዲሆን የፈለገውን እንዳትቀበል እንቅፋት እንዳይሆንብህ በጣም ጥበቃ አድርግ፡፡ በህይወትህ እጅግ ከባድ ፈተና ቢኖርብህ እኔ የምመክርህ በጸሎትህ እንዲህ ማሌን ጀምር ‹‹ ዛሬ እግዚአብሔርን በእምነት እቀርባለሁና ፍርሃትን ሁሉ እቃወማለሁ›› አሁን በድፍረት ጸልይ፣ ከእግዚአብሔር ለመስማት ተጠባበቅ እንዲሁም አንተ ፍጹም ስለሆንክ ሳይሆን እግዚአብሔር መልካም ስለሆነ ለጸሎትህ መልስን ይሰጥሃል፡፡


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ልብህን በሙሉ እምነት ጠብቅ፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon