የፈውስ ቃል
እግዚአብሔር ለሕይወትህ እቅድ አለው፤ እናም በምትጎዳበት ጊዜ ሊፈውስህ ይፈልጋል። በዮሐንስ 10:10 ላይ ኢየሱስ ወደ ምድር የመጣው የተትረፈረፈ ሕይወት ሊሰጠን እንደሆ ይናገራል፣ እናም የዚህ የተትረፈረፈ ሕይወት አካል የሆነው ደግሞ ጤናማና በአካላዊ፣ በመንፈሳዊ፣ በአእምሮ እና በስሜታዊነት ምሉዕ ህይወትህ እንዲኖርህ ማስረገጥ ነው።
እውነታው ግን በሽተኛ መሆን እንደምትችለው ዓይነት ጤንነትን “መያዝ” አልቻልክም፡፡ ለምሳሌ፣ ጉንፋን ከያዘው ሰው አጠገብ ካለህ፣ በጉንፋን ለመያዝ ምንም ነገር አታደርግም። በአካባቢው በመገኘትህ ብቻ ልትያዝ ትችላለህ፤ ምክንያቱም ይህ የበሽታና የበሽታ ባህርይ ነው፡ ፡ ነገር ግን በጤናማ ሰው አጠገብ ልትሆን በመቻልህ የእነርሱ ጤንንት ላታገኝ ትችላለህ፡፡ ስለዚህ ጤናን መምረጥ አለብህ፡፡
ተስፋ በአስቸጋሪ ጊዜያት ውስጥ
ተስፋ የምንጠብቀው አንድ መልካም ነገር እንደሚሆን አርግጠኛ መሆን ነው፡፡ እርሱም በቀጥታ ከእምነታችንና ከምናምንበት ነገር ጋር የተቆራኘና የተዛመደ ነው፡፡ በተስፋ ስንሞላ ሕይወታችን በሰላምና በደስታ ይጥለቀለቃል፡፡
ስማኝ ተስፋ መቁረጥ
ሰይጣን በረቀቀው መንገዱ ሁለንተናችንን ማለትም ሰውነታችንና ነፍሳችንን ከመጨቆን ወደ ኋላ አይልም፡፡
እንደምወዳቸው ንገሯቸው
እግዚአብሔር ይወድሃል!