…እግዚአብሔር የናዝሬቱን ኢየሱስን በመንፈስ ቅዱስ በኃይልም ቀባው፥ እርሱም መልካም እያደረገ ለዲያብሎስም የተገዙትን ሁሉ እየፈወሰ ዞረ፥ እግዚአብሔር ከእርሱ ጋር ነበረና፡፡ (ሐዋ 10፡38) ፡፡
በምድር ላይ ጌታ ኢየሱስ ክርስቶስ ሳለ በነበረው ሠማያዊ ጥሪው ወይም ተግባሩ ማለት እንችላላን፣ በመንፈስ ቅዱስ ኃይል ተቀብቶ በዲያቢሎስ ቀንበር ውስጥ ወድቀው የነበሩት ሠዎች ሁሉ ነጻ ሲያወጣ ነበር፡፡ ያ በእርሱ ላይ ሲሰራ የነበረው ነጻ አውጪ መንፈስ ዛሬም በእኛ በልጆቹ ውስጥ ሆኖ እየሰራ ይገኛል፡፡ እግዚአብሔር ልጆቹ በሀፍረትና በጭቆና መንፈስ ውስጥ ሆነው እንዲመላለሱ ፍፁም ፍቃዱ አይደለም፡፡ ዛሬም ድረስ ከማናቸውም መንፈሳዊ ጭቆና ነጻ የሆነ ህይወት እንዲኖሩ የአባታችሁ የእግዚአብሔር ፍፁም ፍቃድ ነው፡፡
አውርድ