መብራትና ብርሃን

መብራትና ብርሃን

ሕግህ ለእግሬ መብራት፣ ለመንገዴ ብርሃን ነው፡፡ መዝ 119÷105

ከእግዚአብሔር ቃል በላይ የበለጠ ታላቅ መለኮታዊ ኃይል በእግዚአብሔር መንፈስ ቅዱስ መለኮታዊ እስትንፋስ በነብያቱና በደቀመዛሙርቱ በኩል ለእኛ የተሰጠ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ ለማንኛውም ጥያቄ በማንኛውም ጉዳይ ለእኛ መልስ ነው፡፡ መጽሐፍ ቅዱስ በመሠረታዊ መመሪያዎች የተሞላ በሰው ልጆች ባሕሪ ላይ ባለው የእግዚአብሔር ምህረት እውነተኛ ታሪኮችና በግብረ ገባዊ ምሣሌያዊ የበለፀገ ለማንኛውም በምድር ላይ ለሚኖር ሰው ጠቃሚ እውነትና የተሞላ ነው፡፡

መጽሐፍ ቅዱስ ለአንተና ለእኔ የየግል ደብዳቤ ነው፡፡ እኛ ለማወቅ የፈለግነውን ይናገናል፡፡ እግዚአብሔር ግልፅ በሆኑ ምዕራፎችና ጥቅሶች የምናገረን ጊዜያት አሉ፡፡ ይሁን እንጂ እርሱ የተነገረን እርግጥ ከእርሱ ከሆነ የሰማነው ድምፅ ከቃሉ ጋር ይስማማል፡፡

እግዚአብሔር በማንኛውም ሁኔታ ውስጥ በቃሉ ከፈለግነው ይናገረናል፡፡ ደግሞም ይመራናል፡፡ በሕይወቴ ስለ አንድአንድ ነገሮች በጥልቀት ለማወቅ ፈልጌ ስጠይቀው ወደ ቅዱሳት መጽሐፍት ውስጥ የፈለኩት ግልፅ አድርጎ ወደሚያሳየኝ መልስ ይመራኛል፡፡
የእግዚአብሔርን ድምፅ መስማት ማለት በመንፈስ ቅዱስ መመራት መንፈስ ቅዱን ከተሞላው ወደህ እለት እለት እንደተፈጥሮአዊ የሕይወት ሂደት ሆኖኛል፡፡ እግዚአብሔር የመንፈስ ቅዱስን ፀጋ ሥጦታ ለመለመን ለማንም ሰው ይሰጣል (ሉቃ 11÷13 ተመልከት) መንፈስ ቅዱስም የእግዚአብሔርም ቃል እንድንረዳና በሕይወታችን ጥበቡን ይገልጣል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- መጽሐፍ ቅዱስን እንደግል ደብዳቤ ለአንተ እንደተፃፈ አንብብ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon