ራስን ማበረታታት

ስለዚህ ምክንያት እንደሚያቀጣጥል ሰው፣ እጆቼን በመጫን በአንተ ያለውን የእግዚአብሔርን ስጦታ እንድታነሳሳ አሳስብሃለሁ፡፡ –  1ጢሞ 16

እግዚአብሔር ፍቅር ዘላለማዊና በሁኔታ ላይ ያልተመሰረተ ነው፡፡ ፍቅሩን በገለጠልኝ ጊዜ ምን ያህል እንደተደነቁና እንደተደሰትኩ አስታውሳለሁ፡፡ የምፈነዳ ያህል ነበር የተሰማኝ፡፡

ነገር ግን ከቆይታ በኋላ፣ እውነቱ እግዚአብሔር እኔን መውደዱ እውነት እንደሆነ ባውቅም፣ አሁን ግን እንደመጀመሪያው አይነት የፍቅር ስሜት አይሰማኝም፡፡ እንዲህ ያለው ነገር ገጥሟችሁ ያውቃል? አሁንስ ተመሳሳይ ሁኔታ ውስጥ እያለፋችሁ ነው? ከሆነ፣ ያላችሁበትን ሁኔታ በተመለከተ አንድ ማድረግ የምትችሉት ነገር እንዳለ አምናለሁ፡፡

ጳውሎስ ለጢሞቲዎስ በውስጡ ያለውን እሳት ከእንደገና እንዲቀጣጠል ራሱን ማነሳሳት እንዳለበት የነገረው መልዕክት ዛሬ እግዚአብሔር ለእናንተም የሚነግራችሁ መልዕክት ነው፤ ራሳችሁን አነሳሱ! ያረጀና ተመሳሳይ የሆነን ኑሮ በመኖር የድካም ኑሮን መኖር አቁሙ፡፡

ይህን ማስታወስ ያስፈልገናል፤ ህይወትን ለመኖር ስንወስን በስሜት ሳይሆን በፍቅር ነው፡፡ ስለዚህ ሁል ጊዜ ጠዋት ከፈጠረን ከአምላካችነ ጋር ስላለን ግንኙነት እያሰብን በመደነቅ ለመነሳት ዛሬ እንወስን፡፡ ራሳችሁን አነሳሱ፣ በእርሱ በመደነቅም ኑሩ!

የጸሎት መጀመሪያ

እግዚአብሄር ሆይ! ሁል ጊዜ በአንተ እየተደነቅኩ መኖር እፈልጋለሁ፡፡ ባልተነቃቃ ስሜት መኖር አልፈልግም፡፡ አንተን ማወቅ የሚደንቅ ነገር ነው፡፡ አሁን ምርጫዬ ከአንተ ጋር ያለኝን ግንኙነት እያሰብኩ በተነቃቃ ስሜት መኖር ነው፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon