«… ስምዖንም መልሶ፦ አቤቱ፥ ሌሊቱን ሁሉ አድረን ስንደክም ምንም አልያዝንም፤ ነገር ግን በቃልህ መረቦቹን እጥላለሁ አለው» (ሉቃ.5፡5)።
እግዚአብሔር ለእኛ ያዘጋጀው በረከቶችንና አዳዲስ ዕድሎች አሉት። እነዚህ በረከቶችንና እድሎች ለመቀበል ከእርሱ ድምጹን መስማት፣ ለመረዳት መቻልና በዚያው ድምጽ የእምነትን እርምጃ መውሰድ ነው። ይህ አብዛኛውን ጊዜ ለስሜታችን እንደሚሰማን ላይሰራ ይችላል፤ ሊሠራ ይችላል ብለን ላናስብም እንችላለን፤ ወይም አስፈላጊ መስሎ ላይሰማን ይችላል። ነገር ግን በእግዚአብሔር መታመናችንና እርሱን መፍራታችን ከእኛ ግላዊ ፍላጎት ስሜት ወይም ሀሳብ በላይ ታላቅ ነው።
ይህንን በሉቃ. 5 ላይ ትክክለኛውን ምሳሌ እንመለከታለን። ጴጥሮስና ሌሎች ደቀመዛሙርት ሌሊቱን በሙሉ ዓሳ ለማጥመድ ሲሞክሩ አድረው ምንም ነገር አልያዙም። እነርሱ በጣም ተዳክመው ነበር። በእርግጥ ተስፋ ቆርጠው ነበር። አሁን እነርሱ የሚያስፍልጋቸው ጥሩ የምሽት እንቅልፍ እና ምናልባትም ጥሩ ምግብ ያስፈልጋቸዋል። እነርሱ አሁን ሥራቸውን ጨርሰው መረባቸውን አጣጥበው እየሰበሰቡ ነበር። ይህ ለእነርሱ ትልቅ ሥራ ነበር።
ከዚያም ኢየሱስ ወደ ሐይቁ ዳርቻ ቀረበና ብዙ ዓሳዎችን መያዝ ይፈልጉ እንደሆነ እንደገና መረባቸውን ወደ ጥልቁ ውሃ መጣል እንደሚጠበቅባቸው ተናግራቸው። ጴጥሮስም ሌሊቱን በሙሉ ከባድ ሥራ ላይ እንደነበሩና ምንም ነገር እንደላጠመዱና አሁን እነርሱ ተዳክመው እንዳሉ አስረዳ። ነገር ግን አሁን አርሱ ኢየሱስ እንዲያጠምዱ በነገራቸው መሠረት እንደገና ለመሞከር ተስማማ።
ጌታም እንደዚህ ዓይነት አመለካከት ያላቸውን ሰዎች ይፈልጋል። አንድ ነገር እንዳደረገልን ያህል ላይሰማን ይችላል፤ ምናልባትም ይህን ነገር ማድረግ አንፈልግም ይሆናል፤ ምናልባትም መልካም መስሎ ላይታየን ይችላል፤ ይህ ነገር ላይሠራም ይችላል የሚል ፍርሃት ሊኖርብን ይችላል። ነገር ግን እግዚአብሔር ለእኛ ሲናገረን ለመስማትና ለመታዘዝ ፈቃደኛ መሆን ያስፈልጋል።
ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ ምንም እንኳን ስሜታችን ደስተኛ ባይሆንም እግዚአብሔርን ለመስማትና ለመታዘዝ ፈቃደኛ መሆን አለብህ። እርሱ ለአንተ ያዘጋጀልህ ብዙ ትልልቅ ነገሮች አሉትና።