በእርግጠኝነት እግዚአብሔርን ትታመናለህ

በእርግጠኝነት እግዚአብሔርን ትታመናለህ

ስለዚህ የተወደዳችሁ ወንድሞች ሆይ ድካማችሁ በጌታ ከንቱ እንዳሆን አውቃችኋልና የምትደላደሉ የማትነቃነቁም የጌታም ሥራ ሁልጊዜ የሚበዛላችሁ ሁኑ፡፡ 1ቆሮ 15÷58

የጽናት ችሎታችን የሚያመለክተው በጌታ መታመናችንን ነው፡፡ በእግዚአብሔር እታመናለሁ እያል ነገር ግን እየተረበሽኩና እየተገለባበጥኩ ከሆነ በእርግጥ በእግዚአብሔር እየታመንኩ አይደለሁም፡፡ በእግዚአብሔር እታመናለሁ እያልኩ በተስፋ መቁረጥና በጭንቀት መዋጥ በትክክል አለመታመነን ያመለክታል፡፡ በእውነት እግዚአብሔርን ስንታመን ወደ እርሱ እረፍት ውስጥ መግባት ልባችን በእርሱ በማይነቃነቅ ድፍረት ውስጥ እንሆናለን፡፡ በዚህን ጊዜ ጠላት ሙሉ በሙሉ ከመንገዶችና ከሕይወታችን ባይለቅም ሕይወታችን እርሱን በጣም የሚያስቆጣና የሚያናድድ ያደርግበታል፡፡ ምክንያቱም በትላልቅ ችግሮች ውስጥ ሆነን ሳለ በምድር ላይ እግዚአብሔርን በመውደድና በማገልገል በቆየን መጠን ጠላት በእኛ ዙሪያ እያደባ እያለ እንኳ እግዚአብሔር ለመንፈሳዊ ዕድገታችን ካቀደው መካከል መንፈሳዊ ጡንቻዎቻችንን የሚጠነክርበትና ጠላትን ልንቋቋም በተማርነው ልክ ነው፡፡ ሐዋሪያው ጳውሎስ ይህንን በደንብ ተረድቶታል፡፡ እሱ ሰዎች ችግር እንዳይኖራቸው አይፀልይም፡፡ ነገር ግን በጽናት ችግሮችን በመጋፈጥ እንዲፀኑ ይፀልያል፡፡ በእርግጠኝነት እግዚአብሔርን በመታመን እንዲኖሩና አንተ ወደ እረፍቱ እንድትገባ ያንተን ጉዳይ እርሱ ይሠራልሃል አንተ በእርግጥ እርሱን ስትታመን፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- በእርግጥ በእግዚአብሔር ታመን፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon