በእግዚአብሔር ፊት ራስህን አዋርድ

በእግዚአብሔር ፊት ራስህን አዋርድ

‹‹… እላችኋለሁ፥ ከዚያ ይልቅ ይህ ጻድቅ ሆኖ ወደ ቤቱ ተመለሰ፤ ራሱን ከፍ የሚያደርግ ሁሉ ይዋረዳልና፥ ራሱን ግን የሚያዋርድ ከፍ ይላል›› (ሉቃ.18፡14)።

በሉቃ.18፡10-11 ላይ የምናነበው ለመጸለይ ወደ ቤተ መቅደስ ስለሄዱ ሁለት ዓይነት ሰዎች ነው፡፡ አንዱ ፈሪሳዊ ሲሆን ሌለኛው ደግሞ ቀራጭ (ቀረጥ ሰብሳቢ) ነበር፡፡ ኢየሱስ እንዲህ አለ

‹‹… ፈሪሳዊም ቆሞ በልቡ ይህን ሲጸልይ። እግዚአብሔር ሆይ፥ እንደ ሌላ ሰው ሁሉ፥ ቀማኞችና ዓመፀኞች አመንዝሮችም፥ ወይም እንደዚህ ቀራጭ ስላልሆንሁ አመሰግንሃለሁ፤ በየሳምንቱ ሁለት ጊዜ እጦማለሁ፥ ከማገኘውም ሁሉ አሥራት አወጣለሁ አለ።›› ያደረገውንም መልካም ሥራ ሁሉ ይዘረዝር ገባ፡፡

ከዚህ ክፍል በጣም የምወደው ነገር መጽሐፍ ቅዱስ ፈሪሳዊው ወደ እግዚአብሔር ሲጸልይ ነበር አይልም፡፡ ቃሉ የሚለው ሰውዬው ወደ ቤተ መቅደስ ሄደና ነገር ግን ‹‹ በራሱ ፊትና ወደ ራሱ ጸለየ ይላ፡፡ በዚህ ሥፍራ የምናነብበው ለመጸለይ ስለቀረበው ሰው ታሪክ ነው፣ እናም አሁንም ሰውየው ወደ እግዚአብሔር ጸለየ አይለንም፣ አርሱ የተነጋገረው ወደ ራሱ ነው ይላል፡፡ አንዳንድ ጊዜ እኛ ራሳችንም ያንጸልየው ሰዎችን ለማስደነቅ እንደ ሆነ አስባለሁ፣ ምናልባትም ራሳችንን ላለማስደመም ይመስለኛል፡፡ ታማኞች እንሁንና በአንደበተ ርቱዕ ንግግራችን ራሳችንን ልናስደምም እንችላለን፡፡ ከአንድ ሰው ወይም ከብዙ ሰዎች ጋር በመስማማት ሆነን ወደ እግዚአብሔር ስንጸልይና ከእርሱም መስማት ስንፈልግ፤ ሌሎች ሰዎች እየሰበክን እንዳይሆንና የበለጠ መንፈሳዊነትን ለማሳየት እንዳይሆን በጣም ጥንቃቄ ማድረግ አለብን፡፡ ነገር ግን በእውነተኛነት በልባችን ውስጥ ያለውን ለእግዚአብሔር ማሳወቅ አለብን፡፡ መስማማት እጅግ አስደናቂ ኃይል ያለው ነው፣ ነገር ግን ንጹህ መሆን ይገባል አንደሁም ከትህትና ውስጥ ይገኛል፡፡


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔር ሁሉንም በድብቅ የምታደርጋቸውን መልካም ሥራዎች ሁሉ ያያልና እርሱ ዋጋን ይከፍልሃል፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon