አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር በሹክሹክታ ይናገራል

አንዳንድ ጊዜ እግዚአብሔር በሹክሹክታ ይናገራል

እግዚአብሔርም፣ “እግዚአብሔር በዚያ ያልፋልና ወደ ተራራው ወጥተህ በእግዚአብሔር ፊት ቁም” አለው። ከዚያም ታላቅና ኀይለኛ ነፋስ ተራሮቹን ሰነጣጠቀ፤ አለቶችንም በእግዚአብሔር ፊት ብትንትናቸውን አወጣ፤ እግዚአብሔር ግን በነፋሱ ውስጥ አልነበረም፤ ከነፋሱም ቀጥሎ የምድር መነዋወጥ ሆነ፤ እግዚአብሔር ግን በምድር መነዋወጡ ውስጥ አልነበረም። ከምድር መነዋወጡም ቀጥሎ እሳት መጣ፤ እግዚአብሔር ግን በእሳቱ ውስጥ አልነበረም፤ ከእሳቱም ቀጥሎ ለስለስ ያለ ድምፅ ተሰማ። (1 ነገ 19፥11-13)

ከብዙ ዓመታት በፊት አንዳንድ ፈረሶች አሰልጣኞቻቸው “የልጓም ጆሮ” የሚሏቸው ነገሮች እንዳሏቸው ስገነዘብ በጣም ተደምሜ ነበር ። አብዛኞቹ ፈረሶች ለመምራት በአፋችው ዉስጥ የሚገባ ልጓም ቢያስፈልጋቸዉም አንዳንድ ፈረሶች አንድ ጆሮአቸውን የጌታቸው ድምጽ ለመስማት ዝግጁ ያደርጓቸዋል። አንደኛው ጆሮአቸው ተፈጥሮአዊ ለሆኑ ማስጠንቀቂያዎች ክፍት ይሆናል። ሌላው ጆሮአቸው ለሚያምኑት አሰልጣኛቸው ንቁ ይሆናል።

ነቢዩ ኤልያስ እንደዚህ ዓይነት ጆሮ ነበረው። ተፈጥሮአዊ ሁኔታዎች ለመፍራት በቂ የሆኑ ምክንያቶች ሲሰጡት እና እርሱ ግን ከእግዚአብሔርመስማት አጥብቆ በፈለገ ጊዜ፣ በዙሪያው ባለው ጫጫታ እና ግራ መጋባት ዉስጥም ሆኖ ይህን ማድረግ ችሏል። አየህ፣ ዝም ባለው በኣል እና በአንዱ በእውነተኛው አምላክ መካከል በመወራረድ 450 ሀሰተኛ ነቢያትን አሸንፏል። አሁን ክፉዋ ንግሥት ኤልዛቤል በአንድ ቀን ውስጥ እንደምትገድለው

አስፈራርታዋለች። ምን ማድረግ እንዳለበት ማወቅ ነበረበት! በእግዚአብሔር ፊት በተራራ ላይ ቆመ ። ኃይለኛ ነፋስ በተራሮች መካከል ነፈሰ። አስፈሪ የመሬት መንቀጥቀጥ ተከሰተ፤በዙሪያውም እሳት ነደደ፤ ከእሳቱ በኋላ “ረጋ ያለ ትንሽ ድምፅ” መጣ ። የእግዚአብሔር ድምፅ ለኤልያስ የነፋሱ ኃይል፣ የመሬት መንቀጥቀጡ ወይም የእሳቱ ኃይል አልነበረም፤ ነገር ግን በሹክሹክታው ውስጥ ነበር። ኤልያስ እንዲህ ዓይነት ልዩ ጆሮ ነበረው፤ የሰለጠነና ለጌታዉ ንቁ የሆነ፣ ስለሆነም እርሱ እግዚአብሔር ያዘዘውን አደረገ፣ ይህም ሕይወቱን አድኖልለታል ። እግዚአብሔር ዛሬም በለሆሳስና በሹክሹታ ወደ ልባችን ዘልቆ ይናገራል። የተረጋጋዉንና ዝግ ያለዉን መስማት የምትችልበትን ጆሮ እንዲሰጥህ ጠይቀው።


ዛሬ ለአንተ ያለው የእግዚአብሔር ቃል፡ እግዚአብሔርን ንቁ በሆነ ጆሮ አድምጥ።

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon