በእርሱ የሚያምን ሁሉ የዘላለም ህይወት እንዲኖረው እንጂ እንዳይጠፋ እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከመስጠት ድረስ አለሙን እንዲሁ ወዷልና፡፡ – ዮሐ 3፡16
መጽሀፍ ቅዱስ ስለተለያዩ የፍቅር አይነቶች ይናገራል፡፡ፊሊዮ የሚለው የግሪክ ቃል “ጓደኝነት ወይም ጥልቅ የመውደድ ስሜት” ማለት ነው፡፡ሌላው ደግሞ ኢሮስ ሲሆን ለፍቅረኛ የሚሰማን በስሜት የጋለ ፍቅር ነው፡፡ሌላኛው ሶስተኛ አይነት- በጣም ከፍ ያለ የፍቅር አይነት አለ፡፡
አጋፔ እግዚአብሔር ለልጁ እና ለሰው ዘር ያለው የፍቅር አይነት ነው፡፡በዮሐ 3፡16 ላይ እንዳየነው መስዋዕትነትን የሚከፍል ፍቅር ነው፡እግዚአብሔር አንድያ ልጁን እስከመስጠት ድረስ አለሙን እንዲሁ ወዷልና፡፡
በዚህ ርዕስ ላይ መጽሀፍ ቅዱስ ብዙ ተናግሯል፤በግላችሁ ቁጭ ብላችሁ ልታጠኑት የሚገባ ነገር ነው፡፡ሌላው የአጋፔን ፍቅር ጽንሰ ሀሳብ የሚያስተምር ጥቅስ ማቴ 5፡44 ነው፡፡ጠላቶቻችንን እንድንወድና ስለሚያሳድዱን እንድንጸልይ ይነግረናል፡፡
ለእንተ መልካም ለሆኑ ሰዎች መጸለይ ከባድ አይደለም፡፡ለጎዷችሁ ሰዎች መጸለይ ግን ትንሽ የሚከብድ ነገር ነው፡፡ቤተ-ክርስቲያን ከጓደኞቻችሁ ጋር ማሳለፍ ቀላል ነው፡፡ከከፋቸው እና ብቸኛ የሆኑ ሰዎችን ፈልጎ ለተወሰነ ጊዜ እነርሱ የሚሉትን መስማት ግን ከባድ ነው፡፡ይሄ ነው አጋፔ ፍቅር፡፡ጽድቅ የሆነውን ነገር ለማድረግ ምቾታችሁን መሰዋት፡፡
ሰዎችን በመታገስ፣በመረዳት፣የሚያበረታታ ቃል በመናገር ወይንም መናገር በሌለባችሁ ግዜ ባለመናገር “በአጋፔ ፍቅር” ልትወዷቸው ትችላላችሁ፡፡ሰው እንደመሆናችን መጠን በፍጥረታችን ራስወዳድ ነን እና ያለማቋረጥ “እኔስ” እያልን የምንጠይቅ ስለሆንን በራስወዳድነታችን ላይ በአጋፔ ፍቅር ሃይል ጦርነትን ለማወጅ ጊዜው ነው፡፡
መጽሀፍ ቅዱስ ስለፍቅር የሚለውን ስናጠና እና ስንረዳ ለሰዎች በአላማ ጥሩ እና አፍቃሪ ለመሆን ጊዜው ነው ማለት ነው፡፡እናም በእናንተ ያለው አጋፔ ፍቅር ወደሌሎች ይፍሰስ፡፡
የጸሎት መጀመሪያ
ጌታ ሆየይ አጋፔው ፍቅርህ አስደናቂ ነው፡፡በራስ ወዳድነት ላይ ጦርነትን ሳውጅና በአላማ የአጋፔ ፍቅርን ህይወት ለመኖር ስወስን ሀይልን ስጠኝ፡፡