እግዚአብሔር ስለሚረዳን ይናገራል

እግዚአብሔር ስለሚረዳን ይናገራል

በዚያም ቀን ሸክሙ ከጫንቃህ ቀንበሩም ከአንገትህ ላይ ይወርዳል ቀንበሩም ከውፍረትህ የተነሣ ይሰበራል፡፡ ኢሣ 10÷27

እግዚአብሔር በሕይወትህ መፍትሔ በሚያስፈልግህ ጉዳይ ሲነገርህ ጉዳዩን ማቆም ወይም መተው የለብህም፣ የመንፈስ ቅዱስ ኃይልና ችሎታ የሆነውን ቅባት መታመን አለብህ፡፡ እርሱ አንተን የያዘህን ለመስበር ይችላል፡፡ ችግርህን እንድስማማና ተቻችለህ ለመኖር ተቃውመህ ትግሉን ካላቆምክ በራስህ ሙከራ ነገሩን ለመለወጥ መሞከር ያለ እግዚአብሔር ቅባት መስበር የሚቻል አይደለም፡፡

አብዛኛውን ጊዜ እኛ ነገሮችን በራሳችን ጊዜ ለማድረግ እንፈልጋለን፡፡ ከዚያም የተነሣ ያለ እግዚአብሔር ቅባት ስለሆነ ታግለን ታግለን እንደክማለን፡፡ ለምሳሌ አንዳንድ ጊዜ ጉዳዮችን ባለው ጉልበት ለማስተካከል የሚሞክርበት አጋጣሚዎች አሉ፡፡ ነገር ግን እግዚአብሔር ፊት በመፀለይ እግዚአብሔር በልቡ የሞላውን ሰው እንዲዘጋጅ መፍቀድ ብልህነት ነው፡፡ የእግዚአብሔርን የጊዜ ሠሌዳ ሲጠብቅ ነገሩ በእግዚአብሔር ቅባት ተሰርተው አገኛለሁ፡፡ እኔ በሕይወቴ የተማርኩት በአንዳንድ ጉዳዮች ላይ እንዲሰራ ሲፈቅድ እንዲሁም ነገሩን ትቼ የእግዚአብሔርን ጊዜ እንድጠብቅ ሲነግረኝ ለእርሱ እተዋለሁ፡፡ እንደሁም የሚያናድድ ገጠመኞችም አሉኝ አንዳንድ ነገሮችን ደጋግሜ እሞክርና ያለ እግዚአብሔ እርዳታና ጊዜ ነገሮችን ለመለወጥ በከንቱ እሞክራለሁ፡፡ የእግዚአብሔር ቅባት መኖሩን እርግጠኛ መሆን ለማንኛውም ጉዳይ መረጋገጥ ለሕይወታችን ወሳኝ ነገር ነው፡፡

እግዚአብሔር አንድ ነገር ሕይወታችንን የሚለወጥ ማለት መሆኑን ሲያሳምነን እርሱ እንድንገጥመው እያዘጋጀን ነው፡፡ እኛ እንዳልተዘጋጀን በሰማን ነገር ግን እርሱንና የእርሱን ጊዜ ትክክለኛና የእርሱ ቅባት የእኛን ሙሉ ነፃነት የጋረደውን ለመስበር አለ፡፡ እኔ በሕይወቴ እንዲህ ማለት ተምራለሁ፡፡ ጌታ ሆይ እኔ ዝግጁ እንደሆንኩ አይሰማኝም አንተ ግን ጊዜው አሁን ነው ካልክ እኔ አንተን እታመናለሁ፡፡ ያንተ ኃይል ከእኔ ጋር እንደሆነና ለአንተ ፈቃድ ታዛዥ ነኝ እለዋለሁ፡፡ ልክ በእምነት እርምጃ በመውሰድ በጉዳዩ ላይ መሥራት ስትጀምር የእርሱን ጥበብ፣ ፀጋ፣ ኃይል እና ችሎታ የሚያስፈልግህ ይቀርቡልሃል፡፡


ዛሬ የእግዚአብሔር ቃል ለአንተ፡- ዛሬ እርሱ እንድታደርግ ካንተ የሚፈልገውን እስከሚመጣ ቀን ድረስ አታቋርጥ፡፡

Facebook icon Twitter icon Instagram icon Pinterest icon Google+ icon YouTube icon LinkedIn icon Contact icon